ሶርያ በጦርነቱ 226 ቢሊዮን ዶላር አጥታለች

 

ሶሪያ በጦርነት እየተናጠች ነው፡፡

የሰባዓዊ መብት ቀውሱ ተባብሷል፡፡

ባለፉት ስድስት ዓመታት በሶሪያ በተካሄደው የእርስ በእርስ ጦርነት ሀገሪቱ በአጠቃላይ 226 ቢሊዮን ዶላር የከሰረች መሆኑን የዓለም ባንክ ጥናት አመልክቷል፡፡

ይሄው ጥናት ሶርያ በጦርነቱ 320 ሺህ ዜጎቿን በሞት የተነጠቀች መሆኗን እንደዚሁም ከአራት ሚሊዮን በላይ ህዝቧ ደግሞ በስደት ቀየውን ጥሎ የተበታተነ መሆኑን ያመለክታል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘም 538 ሺህ የስራ እድልም ከኢኮኖሚው የቀነሰ መሆኑን ዘገባው ጨምሮ ይገልፃል።

 

ምንጭ፡ቢቢሲ

 

 

Advertisement