በወባ ትንኝ ደም ወንጀለኞችን ማግኘት እንደሚቻል ያውቃሉ?

አንድ ወንጀለኛ የሰው ህይወት ካጠፋ እራሱን ለመደበቅ ሲል የእጅ አሻራውን፤ የእግር ዱካውን አጥፍቶ ያለምንም ማስረጃና ምስክር ሊኖር ይችላል፡፡

 ይሁንና ወንጀለኛው ወንጀሉን በፈጸመበት አካባቢ ላይ በወባ ትንኝ ተነድፎ ከነበረ ማንነቱን ለመለየት የሚያስችል ግኝት ላይ ደርሰናል ብለዋል ተመራማሪዎቹ፡፡

 የናጎያ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች እንደሚገልጹት ከሆነ ወንጀለኛው በወባ ትንኟ ከተነደፈ በኋላ ባሉት 48 ሰዓታት ውስጥ የግለሰቡን ማንነት በመለየት በቀጥጥር ስር ማዋል ይቻላል፡፡

 የምርመራ ሂደቱም በወባ ትንኝ ውስጥ የተገኘው ዘረ መል የግለሰቡን ማንነት ስለሚያሳውቅ ለወንጀል መርማሪ ፖሊሶችም ቀላል መፍትሄ እንደሚያመጣላቸው ነው የተመራማሪዎቹ ቡድን መሪው ቶሺሚቺ ያማማቶ የገለጹት፡፡

 ይህን የምርመራ ዘዴያቸውን በፍቃደኛ ግለሰብ ላይ በመሞከር በወባ ትንኝ ውስጥ በተገኘ ደም ዘረመል ማንነቱን መለየት እንዳስቻላቸው ተናግረዋል፡፡

 

ምንጭ፡ ዴይሊ ሜይል

 

Advertisement