ቻይና በታሪኳ ለመጀመሪያ ግዜ በጅቡቲ ወታደራዊ ቀጠና አቋቋመች- China sends troops to Djibouti, establishes first overseas military base

ቻይና ከግዘቷ ውጭ እንዲህ አይነት የጦር ቀጠና ስታቋቁም የመጀመሪ ሲሆን በምስራቅ አፍሪካ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታን ለማግኘት ነው ተብሏል፡፡

ይህንንም ተከትሎ ሁለት የጦር መርከቦች ከዚንጂያንግ ወደብ ወደ ጂቡቲ የሚወስዳቸውን አቅጣጫ ይዘዋል ነው የተባለው፡፡

የጦር መርከቦቹ ከያዟቸው ግዙፍ የጦር መሳሪያዎች በተጨማሪ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ወታደሮችም ጭነዋል፡፡

ቻይና በቀጠናው የጦር ሰፈር ስመሰርት አለምን ለመቆጣጠር አይደለም ብላለች፡፡

አሁን ላይ አሜሪካ;ፈረንሳይና ጃፓን ቀደም ብለው በጅቡቲ የጦር ሰፈር የመሰረቱ ሃገራት ናቸው፡፡

ምንጭ፡ሲ ኤን ኤን

 

Advertisement