በሊቢያና በሶሪያ ለተፈጠረው ቀውስ ተጠያቂዋ ኳታር ናት – ግብጽ

 የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳማህ ሹኩሪ እንዳሉት ኳታር አክራሪ እስላማዊ ቡድኖችን በማቋቋምና በመደገፍ በሊቢያና በሶሪያ ላለው ፍጅት ተጠያቂናት ብለዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በአውሮፓና ክርስቲያን ግበጻውያን ላይ ሲደርሰ ለነበረው የሽብር ጥቃት ኳታር እጇ እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

በተለይ በግበጽ ክርስቲያኖች ለይ ለደረሱት የሽብር ጥቃቶች ሃላፊነቱን መውሰድ አለባት ነው ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ

ከዚህ ባለፈ ዛሬ በመካከለኛው ምስራቅ በጦርነት ህጻናት ሲሞት እናቶች ሲሰቃዩ ስትመለከቱ ከጀርባ ኳታር አለች ማለት ነው ብለዋል ሳማህ ሹኩሪ

ኳታር ሰሞኑን ከባህረ ሰላጤው ሙስሊም ሃገራት ጋር እሰጣ ገባ ውስጥ መግበቷን  ተከትሎ ስሟ ከሽብርተኝነት ጋር እየተያያዘ ይገኛል

ምንጭ፡ሲ ኤን ኤን

 

Advertisement