ባል እራቴን አዘግይተሽብኛል በሚል ሚስቱን ገደለ- Indian man kills wife over dinner delay

በሃገረ ህንድ ነው ባለፈው ቅዳሜ አሾክ ኩመር የተባሉ የስድሳ ዓመት ኣዛውንት  አመሻሽተው አልኮል ቢጤም ቀማምስው ወደ ቤት ይገባሉ፡፡

ሱናይና የተባሉት ባለቤታቸው በሁኔታው ደተኛ አልነበሩም፡፡

በንግግር መሃል ሃይለ ቃል ይነጋገሩና ሚሰት ወደ ማብሰያ ክፍል እራት ለማቅረብ ይገባሉ፡፡

በዚህ ማሃል ባል እራቴ ዘገየብኝ በሚል ምክንያት የ55 ዓመት እድሜ ያላቸውን ሚስታቸውን ተኩሰው ገድለዋል፡፡

ሟች አፋጣኝ የህክምና እርዳታ ቢደረግላቸውም ሊተርፉ አልቻሉም፡፡

ባል በድርጊታቸው መጸጸታቸውን ለፖሊስ ገልጠዋል፡፡

ምንጭ-ቢቢሲ

 

Advertisement