በየቀኑ ብርቱካን መመገብ ለአዕምሮ መቃወስ የመጋለጥ እድልን በሩብ ይቀንሳል ተባለ

በየእለቱ ብርቱካን መመገብ ለአዕምሮ መቃወስ የመጋለጥ እድልን እንደሚቀንስ በጃፓን የቶሁኩ ዩኒቨርሲቲ የተደረገ ጥናት አመላከተ።

 ብርቱካን ብቻ ሳይሆን ማንኛውንም ሲትሪክ አሲድ የምናገኝባቸው እንደ ወይን ፍሬ እና ሎሚ ያሉ ፍራፍሬዎችን መመገብ ሊድን የማይችል የአዕምሮ ህመምን በሩብ ይቀንሳል ብሏል ጥናቱ።

 የሲትሪክ አሲድ ኖቢሌቲን የተሰኘ ኬሚካል መያዙን በርካታ ጥናቶች አመልክተዋል።

 ይህ ኬሚካል በእንሰሳት ላይ ተሞክሮ የመርሳት ችግርን እንደሚከላከል ተረጋግጧል።

 በቶሁኩ ዩኒቨርሲቲ የተደረገውና በብሪቲሽ ጆርናል ላይ የወጣው ጥናት ግን ሲትሪክ አሲድ የያዙ ፍራፍሬዎች ለአዕምሮ ቀውስ ለተዳረጉ ሰዎች ያላቸውን ሚና ተመልክቷል።

 ተመራማሪዎች ከ13 ሺህ በላይ በመካከለኛ እና በአዛውንት እድሜ ላይ የሚገኙ ወንዶች እና ሴቶችን የፍራፍሬዎች አመጋገብ እና አሁናዊ ጤንነታቸውን ለበርካታ አመታት አጥንተዋል።

 በዚህም በየቀኑ ሲትሪክ አሲድ ያላቸው ፍራፍሬዎችን የሚመገቡ ሰዎች በሳምንት ከሁለት ጊዜ በላይ ከሚመገቡት ጋር ሲነፃፀሩ ለአዕምሮ ቀውስ የመጋለጥ እድላቸው 23 በመቶ እንደሚቀንስ ተረጋግጧል።

 የጥናቱ ውጤቱ ብሪታኒያውያን ለከፍተኛ የአዕምሮ መቃወስ ችግር መጋለጣቸው በተነገረ ማግስት ነው ይፋ የሆነው።

 በለንደን ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ እና ሊቨርፑል ዩኒቨርሲቲ ባደረጉት ጥናት በእንግሊዝ ብቻ ለአዕምሮ መቃወስ የሚዳረጉ ሰዎች ቁጥር በ2040 1 ነጥብ 2 ሚሊየን እንደሚደርስ አመላክቷል።

 በብሪታንያ ምንም እንኳን ለአዕምሮ ቀውስ የሚዳረጉ ሰዎች ቁጥር በየአመቱ በ2 በመቶ እየቀነ ቢመጣም ለቀጣዮቹ 20 አመታት ከበሽታው ጋር የሚቆዩ በእድሜ የገፉ ሰዎች እየጨመረ ይሄዳል ነው የተባለው።

 ምንጭ: www.dailymail.co.uk/

Advertisement