በአሜሪካ የስድስት ዓመት ልጃቸውን በቀበቶ የገረፉ ኢትዮጵያውያን ባልና ሚሰት ክስ ተመስርቶባቸዋል

ነዋሪነታቸውን በአሜሪካ ያደረጉት እፀገነት ተክለፂሆንና በላይነህ አጋቶ በስድስት ዓመት ልጃቸው ለይ ባደረሱት አካላዊ ጥቃት ነው ፍርድ ቤት የቀረቡት፡፡

ወንድ ልጃቸውን በቀበቶ ከመግረፋቸውም በተጨማሪ ቤት ውስጥ ብቻውን እንዲሆን አድርገዋል ነው ተባለው፡፡

ይህንንም ተግባር ጎረቤቶች ተመልክተው ለፖሊስ አሳወቀዋል፡፡

ወላጆቹ ስለ ጉዳዩ ለጠየቃቸው ፍርድ ቤት በሃገራቸው ኢትዮጵያ እንዲህ አይነቱ ልጅን የመቅጣት ተግባር የተለመደ ነው ብለዋል፡፡

ምንጭ-AJC news

 

Advertisement