SPORT: ሊዮኔል መሲ ከሰርጉ የተረፉ ምግቦችና መጠጦችን በእርዳታ ለገሰ

የባርሴሎናው ኮከብ ሊዮኔል መሲ ከሰርጉ በኋላ በሰርጉ ላይ ጥቅም ላይ ያልዋሉ ምግብና መጠጦችን ለእርዳታ ድርጅቶች በመለገስ ምንም ዓይነት ምግብ እና መጠጥ እንዳይወገድ ማድረገ መቻሉን የመሲ የትውልድ ከተማ የሆነችው ሮዛሪዮ የምግብ ማከማቻ ዋና ኃላፊ የሆኑት ፓብሎ አልጋሪያን ገልፀዋል።

የእግርኳሱ ዝናኛ ሰው መሲ ባለፈው ሳምንት ከረጅም ጊዜ ፍቅረኛው አንቶኔላ ሮኩዞ ጋር በትውልድ ሃገሩ በትዳር ተሳስሯል።

የባርሴሎና ክለብ አጋሮቹ ኔይማር፣ ልዊስ ስዋሬዝ እና ጄራርድ ፒኬ እንዲሁም ዳኒ አልቬስ፣ ሰርጂዮ አግዌሮ፣ ሴስክ ፋብሪጋዝ፣ ኤንጅል ዲ ማሪያ፣ ዣቪ እና ካርሎስ ፑዮል ባለፈው ሳምንት አርብ በተከናወነውና በሃገሪቱ መገናኛ ብዙሃን “የክፍለ ዘመኑ ምርጥ ሰርግ” የተሰኘውን የጋብቻ ስነስርዓት ለማድመቅ በስፍራው ከተገኙ በርካታ ከዋክብት መካከል ይጠቀሳሉ።

ከዚህ ድል ካለ ሰርግም ጥቅም ላይ ያልዋሉ በርካታ ምግብና መጠጦች የተተርፈረፉ ሲሆን፣ ምስጋና በአምስት ጊዜያት የባሎን ዶር አሸናፊው እና በባለቤቱ ይሁንና እነዚህ የተረፉ ምግቦች ወደቆሻሻ ማከማቻ ሳይወገዱ ቀርተዋል።

“ወደምግብ ማከማቻችን ደርሰው ወስደናቸዋል።” ሲሉ ኃላፊው አልግሪያን ለኤልፍ ሚዲያ ተናገረው “ምን ያህል መጠን እንዳላቸው እስካሁን አላወቅንም።

“ለሰርጉ አዘጋጆች ለስላሳ መጠጦችንና ብስኩትና ጥብሳጥብሶችን ብቻ እንደምንቀበል ነግረናቸዋል። ነገር ግን የአልኮል መጠጦችን ግን ልንቀበል ስለማንችል ወደገንዘብ እንቀይራቸዋለን።” ሲሉ ተናግረዋል።

የ30 ዓመቱ መሲ ከአዲሷ ሙሽራው እና ሁለት ልጆቹ ጋር በመሆን የጫጉላ ጊዜውን እያሳለፈ የሚገኝ ሲሆን፣ ከጫጉለው ሲመለስ ደግሞ በባርሴሎና እስከ2021 ድረስ የሚያቆየውን አዲስ የኮንትራት ስምምነት የሚፈርምም ይሆናል።

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

Advertisement