በሜክሲኮ ወይኒ ቤት በእስረኞች መካከል በተፈጠረ ግጭት 28 እስረኞች ሞቱ።

                                            

በደቡብ ምእራብ ሜክሲኮ በአካፑልኮ ከተማ በሚገኘው ወይኒ ቤት በተከፋፈሉ የእስረኞች ቡድን መካከል በተፈጠረ ግጭት ነው የሞት አደጋው የደረሰው።

ቢቢሲ ከስፍራው እንደዘገበው በእስር ቤቱ ማብሰያ ውስጥ ሳይቀር አስከሬኖች ወድቀው ታይተዋል።

የወይኒ ቤቱ አስተዳዳሪዎች እንዳሉት ከሞቱት እስረኞች መካከል በጦር መሳሪያ የተገደለ የለም።

የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ የቻለው የተነሳወን ገጭት ለማምለጥ እስረኞች እርስ በራሳቸው በመተፋፍጋቸው ነው። 

ከዚህ በተጨማሪ በአደገኛ ቡድኖች መካከል የተፈጠርው ግጭት በምን ምክንያት እንደሆነ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም፡፡

እስር ቤቱ የአለማችን አደገኛ እስር ቤቶች መካከል ቀዳሚው ነው።

Advertisement