NEWS: በሺህ የሚቆጠሩ ዶሮዎች የኦስትሪያ አውራ ጎዳናዎችን ዘጉ::120 የአደጋ ሰራተኞች ደሮዎቹን ለመያዝ ተሳትፈዋል::

                                 

በኦስትሪያ አንድ የሚያንቀላፋ የጭነት መኪና ሾፌር ከእንቅልፉ ብዛት የተነሳ መኪናው መንገድ ስቶ ድልድዩ አምድ ጋር በመጋጨቱ ጭኗቸው የነበሩት ደሮዎች ከሳጥኑ ወጥተው መንገድ በመዝጋታቸው ነው፡፡

መኪናው ለእርድ ይዟቸው ይጓዝ የነበሩትን 7ሺህ 500 ደሮዎች በእንቅልፋሙ ሹፌር ምክንያት የታሰበብት ቦታ ሳይደርሱ መንገድ ላይ ወጥተው አውራ ጎዳናውን በማጨና ናነቃቸው አውራ ጎዳናው ለተወሰነ ጊዜ እንዲዘጋ ምክንያት ሆኗል፡፡
ጉዳዩ የተፈጸመው በሊንዝ ኤዋን በተባለ አውራ ጎዳና ላይ ነው፡፡

 ነጻነታቸውን ያወጁት በሺዎች የሚቆጠሩ ደሮዎች በአውራ ጎዳናው ላይ ሲሯሯጡ የታዩ ሲሆን ባለሥልጣናት የመንገዱን ክፍል እንዲዘጉ ተገደዋል፡፡ ዶሮዎቹንም ለመያዝ ያደርጉት የነበረው ሩጫ እንደትርኢት ነበር ሲል ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡

በጉዳዩ ምክንያት ከባድ የትራፊክ መጨናነቅ እንደነበር ተዘግቧል፡፡ 120 የአደጋ ሰራተኞች ደሮዎቹን ለመያዝ የተሳተፉ ሲሆን በአደጋው የተወሰኑ ደሮዎች ላይ ጉዳት ከመድረሱ ውጭ በሰዎች ላይ ጉዳት አልደረሰም፡፡

ምንጭ፡-ሲኤን ኤን

Advertisement