የሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ከአደጋ ተጋላጭ የዓለም ቅርስነት ዝርዝር ውስጥ ወጣ

                        

  በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የተመዘገበው  የሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ ከአደጋ ተጋላጭ የዓለም ቅርስነት ዝርዝር ውስጥ እንዲወጣ የዓለም ቅርስ ኮሚቴ ወሰነ፡፡

የሰሜን ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ እ.ኤ.አ በ1978 በዩኔስኮ የዓለም የተፈጥሮ ቅርስነት የተመዘገበ ሲሆን እ.ኤ.አ በ1996 በዩኔስኮ የአደጋ ተጋላጭ የአለም ቅርስ ዝርዝር ውስጥ ተካቶ ቆይቷል፡፡

የአለም ቅርስ ኮሚቴ በፖላንድ ክራከው እያካሄደ ባለው 41ኛ መደበኛ ስብሰባ ግን በፓርኩ አያያዝና አስተዳደር ዙሪያ ባለፉት ጊዜያት በተሰራው ስራ ውጤት መምጣቱን በመገምገም ፓርኩ አደጋ ውስጥ ከሚገኙ የአለም ቅርሶች ዝርዝር ውስጥ እንዲሰረዝ ወስኗል።

በተለይ በፓርኩ ውስጥ የሚገኙ እንደ ዋልያ እና ጭላዳ ዝንጀሮ ያሉ ብርቅዬ እንሰሳትን ጠብቆ ለማቆየት የሚያስችልና ፓርኩን የተሻለ የቱሪስት ቦታ ለማድረግ የተሰራው ስራ በዓለም ቅርስ ኮሚቴ ተገምግሞ ነው ከአደጋ ተጋላጭ ዝርዝር ውስጥ የወጣው፡፡

ምንጭ፡- http://whc.unesco.org

Advertisement