በ13ኛው የአፍሪካ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና የሚሳተፈው ቡድን ተሸኘ::

                                         

በ13ኛው የአፍሪካ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን ወክሎ የሚወዳደረው ቡድን ትናንት አሸኛኘት ተደርጎለታል።

በሽኝት ስነ ስርዓቱ ላይ የወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ተወካዮች፣ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ዋና ዳይሬክተር አቶ ታምራት በቀለና አትሌት ደራርቱ ቱሉ ተገኝተዋል።

አትሌቶች፣ አሰልጣኞችና የቡድኑ የቴክኒክ ቡድን መሪ በሆቴል በቆዩባቸው የዝግጅት ጊዜያት ጥሩ የስልጠና ቆይታ ማድረጋቸውንና በውድድሩም ውጤታማ ሆነው ለመመለስ ቁርጠኛ አቋማቸው መሆኑን በሽኝቱ ወቅት ተናግረዋል።

በዚህ ፕሮግራም ላይ ክብርት ዶ/ር ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ፥ ካላት ተሞክሮ በመነሳት አትሌቶቹ ምን መስራት እንደሚገባቸው መልዕክት አስተላልፋለች።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ ለልኡካን ቡድኑ አባላት የመልካም ምኞት አስተላልፈዋል።

አትሌቶች ከአሰልጣኞቻቸው ጋር የሚኖራቸው ግንኙነት በመተሳሰብና በመደማመጥ ላይ የተመሰረተ እንዲሆንም አሳስበዋል።

13ኛው የአፍሪካ ወጣቶች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከሰኔ 21  እስከ ሀምሌ 25 2009 በአልጀሪያ ቴልሚስ ከተማ እንደሚካሄድ ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።

ምንጭ:- FBC

 

Advertisement