ማንበብ ለጤናችን በምን መልኩ ይጠቅማል? – Health Benefits of Reading

                                              

ማንበብ እውቀትን ከምንቀስምበት መንገዶች ውስጥ አንዱ እና ዋነኛው ነው።

ከዚህ በዘለለ ግን ማንበብ ለጤንነታችንም ጠቀሜታዎችን ይሰጠናል የሚሉት የስነ ልቦና ባለሙያዎች፥ ማንበብ በቀላሉ የራሳችንን እና የሌሎችን ልብ ለመረዳት ያስችለናል ብለዋል።

ሰዎች የሚያነቡት የተለያየ አይነት መፅሃፍ ነገሮችን በቀላሉ እንዲፈቱ እና እንደሚለከቱ ይችላሉ፤ ይህም ኑሯቸው ጤነኛ እና የተስተካከለ እንዲሆን ይረዳል ሲሉም ባለሙያዎቹ ይናገራሉ።

ለምሳሌ ልበወለዳዊ መጽሃፍትን የሚያነቡ ሰዎች ሌሎች ሰዎችን በቀላሉ እና በተሻለ መልኩ ሊረዱ ይችላሉ የሚሉት በቶሮንቶ ዩኒቨርሲቲ የስነ ልቦና ባለሙያው ኬይት ኦታሌይ።

ማንበብ የፍቅር ህይወታችን እና የቤተሰቦቻችን ህይወት እንዲሻሻል እንዲሁም በስራ ቦታችን ላይ ከባልደረቦቻችን ጋር ያለን ግንኙነት መልካም እንዲሆን ያደርጋልም ብለዋል።

በቤተ ሙከራ በተደረገ ምርምርም በተለይም ልበ ወለድ መጽሃፍትን የሚያነቡ ሰዎች የሌሎች የሰዎችን ችግር በቀላሉ መረዳት እንደሚችሉ ያሳያል።

ከዚህ ቀደም የተሰሩ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ ደግሞ ማንበብ የአእምሯችንን የነርቭ ኔትዎርክ አቅም እንዲጨምር በማድረግ ውስብስብ የሆኑ ነገሮችን በቀላሉ እንድንረዳ ያደርጋል።

በጣም አምባቢ ባንሆንም በመጠኑ የምናነብ ከሆነ ለአእምሯችን ነርቭ ጠቀሜታ አለው ተብሏል።

እንዲሁም ማንበብ አእምሯችን በአግባቡ ስራውን እንዲያከናውን ያግዛል ሲሉም የስነ ልቦና ባለሙያዎቹ ያብራራሉ።

ከዚህ በተጨማሪም ጭንቀት የሚያስቸግረን ከሆነ መጽሃፍትን ማንበብ በውስጣችን ላይ ያለው የጭንቀት መጠን እንዲቀንስልን እንደሚያደርግም የስነ ልቦና ባለሙያዎቹ ይናገራሉ።

ማንበብ ለከፍተኛ የመርሳት በሽታ (አልዛይመር) የመጋለጥ እድልንም እንደሚቀንስ ነው ባለሙያዎቹ የሚናገሩት።

ምንጭ፦ cnn.com