ተመራማሪዎች ከመደበኛው ጊዜ ቀድመው የሚወለዱ ህጻናትን የሚያሳድግ ሰው ሰራሽ ማህፀን ሰሩ – Reserchers Invent Artificial Womb Wich Fanction as a Temporary Womb For Preterm Birh

                                             

የፊላደልፊያ የህጻናት ሆስፒታል እና የኤደንብራ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎች ከመደበኛው የወሊድ ጊዜ ቀድመው የሚወለዱ ህጻናትን በፅንስ መልኩ እንደ አዲስ በመደበኛ ሁኔታ የሚሳድግ አዲስ ሰው ሰራሽ ማህፅን ሰርተዋል፡፡

ተመራማሪዎቹ “ባዮ ባግስ” የተባለውን ማህፀን የ23 ሳምንት እድሜ ካለው የሰው ጽንስ ጋር እኩል እድሜ ያለው የበግ ሽል እንዲያሳድግ ሞክረውት ውጤታማ ሆኗል ብለዋል።

ሽሉ ባግስ ከተሰኘው ሰራሽ ማህጸን ውስጥ ሲንቀሳቀስ የሚያሳይ ቪዲዮም ተመራማሪዎቹ ለቀዋል፡፡

ሙከራውም ያለ እድሜያቸው ከ21 እስከ 23 ሳምንት ባለው የእርግዝና ጊዜ የሚወለዱ እና መደበኛ የአካል እድገት የማይታይባቸው ህጻናት ከእናታቸው ማህፀን ውጭ በቂ የሆነ እድገት እንዲኖራቸው ለማድረግ ያለመ ነው።

ይህ ከመደበኛው የእንስሳት ሽል ማሳደጊያ ወይም ኢንኩቤተር የተለየ ሆኖ የተሰራው ሰው ሰራሽ ስነህይወታዊ ማህፀን፥ አስጊ ሁኔታ ውስጥ ወይም በእድገት አለመመጣጠን ምክንያት ህመም ውስጥ ያሉ ፅንሶችን በእንክብካቤ ለማሳደግ ይረዳል ተብሎለታል፡፡

ሰው ሰራሽ ማህፀኑ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታትም ወደ ሙከራ ተግባር እንደሚገባ ነው የተተነበየው፡፡

ማህፀኑ ሙሉ የእርግዝና አገልግሎቶችን ወይም ሙሉ ፅንስ የማሳደግ አገልግሎት የማይሰጥ ሲሆን፥ ከመደበኛው ወሊድ ጊዜ ቀድመው የተወለዱ ህጻናትን እንደገና በፅንስ መልኩ የቀራቸውን እድገት እንዲያሟሉ የማድረግ ተግባር ነው የሚሰጠው፡፡

በሰውሰራሽ ማህፀኑ ውስጥም ህጻኑ ምቹ ሁኔታ ተፈጥሮለት አይኖቹን እንዲገልጥ፣ እንደማንኛውም ፅንስ እንዲንቀሳቀስ፣ እንዲተነፍስ እና ምግብ እንዲገኝ ሆኖ የተሰራ ነው፡፡

ምንጭ፡-ደይሊ ሜይል

Advertisement