ስለ ልብ እውነታዎች – Facts About the Heart

                                                   

ልባችን በቀን 100,000ሺህ ጊዜ ይመታል፡፡ በደቂቃ ደግሞ 1.5 ጋሎን ደም የሚረጭ ሲሆን የቀኝ የልብ ክፍላችን ወደ ሳምባችን ሲረጭ የግራ የልብ ክፍላችን ደግሞ ወደተለያዩ የሰውነት ክፍሎች ይረጫል፡፡
-75 ትሪሊዮን የሚሆኑ ሴሎቻችን ደምን የሚቀበሉት ከልባችን ነው፡፡
-የሴቶች ልብ ከወንዶች ይልቅ በፍጥነት ይመታል፡፡ በዚህም የወንዶች በአማካኝ በደቂቃ 70 ጊዜ ሲመታ የሴቶች ደግሞ በአማካኝ 78 ይደርሳል፡፡
-አንድ በማህፀን ውስጥ ያለ ፅንስ 4 ሳምንት ከሞላው ጀምሮ እስከ ህይወቱ ማብቂያ ድረስ ልቡ ይመታል፡፡
-በየቀኑ ልባችን የሚፈጥረው ሃይል 20 ማይል ከባድ መኪና ማስነዳት ይቻለዋል፡፡
-ከየትኛውም የሰውነታችን ጡንቻ ይልቅ ልባችን የበለጠ እንቅስቃሴ ያደርጋል፡፡
-በምግብ ማብሰያ ቤት ውስጥ ያለ ቧንቧ ለ45 ዓመታት ክፍት ቢደረግ ልባችን በህይወት ዘመናችን ከሚረጨው ደም ጋር እኩል ነው፡፡
-አትክልት እና ጥቁር ቸኮሌትን መመገብ የቻሉ ሰዎች 19 በመቶ የልብ ህመምን መቀነስ ይችላሉ፡፡

ምንጭ :-ጤና

Advertisement