ለፈንገስ ወይም ጭርት በሽታዎች የሚሆኑ የቤት ውስጥ መፍትሄዎች።

 

 

የፈንገስ ወይም ጭርት በሽታ በማንኛውም የሰውነታችን ክፍል ሊከሰት ይችላል።  ነገር ግን አብዣኛውን ጊዜ የሚገኘው በአውራ  ጣቶች ወይም በተቀሩት ጣቶቻችን (የእግር ጮቅ) እና በእግር መካከል ነው። ጭርት እና (ቆርቆሮ መሰል ነጭ መልክ ያለው በአናት ላይ የሚታይ) በፈንገስ የመመረዝ ውጤት ነው። የተመረዘው ስፍራ በየቀኑ በውሃ እና በሳሙና መታጠብሲገባው ደረቅ መሆንና በዘይት (ከታች እንደተመለከተው) መታከም አለበት። ከተቻለ ለንፁህ አየርና ለፀሃይ ብርሃን ማጋለጥ ያስፈልጋል። ከተፈጥሮ የተሰሩ ልምሶችን ማለትም የጥጥ ልብሶችን መልበስ ትልቅ ለውጥ ያመጣል። ሁልጊዜ የበሽታው ምልክት ከጠፋ በኋላ እንኳን ለሁለት ሳምንታት ያህል ህክምናው መቀጠል ይኖርበታል።

  • ነጭ ሽንኩርት

 

 የነጭ ሽንኩርቱን ዘይት በሽታው ባለበት ቦታ ላይ ማሸት።

    • ይህንን ዘይት ለእግር ጮቅም ይጠቀሙ።
    • በአማራጩ በአውራ ጣት መካከል አዲስ የተሠነጠቀ ነጭ ሽንኩርት ሊደረግ ይችላል።

 

 

 

 የጉሎ ዘይት ወይም የዘምባባ ዘይት እና ካሲያ አላታ

 

 የካሲያ አላታ (የጭርት ቅጠል) ተክል
 
    • የካሲያ አላታን (የጭርት ቅጠል) አዲስ ቅጠል መውቀጥና ከተመጣጣኝ የጉሎ ዘይት ጋር መደባለቅ። የጉሎ ዘይት ካልተገኘ የዘምባባ ወይም ሌላ የአትክልት ዘይት መጠቀም።
    • አዲስ በማዘጋጀት በቀን ሦስት ጊዜ መጠቀም

 

 

ፓፓያ ፣ ዘይት እና ደን መሳይ የጭርት ቅጠል 

 

    • አንድ እፍኝ ያህል አዲሱን ደን ቅጠል መሰል የጭርት ቅጠል መፍጨት።
    • የጥሬ ፓፓያ ፍሣሽ 10 ጠብታ ያህል እና አንድ የሾርባ ማንኪያ የጉሎ ወይም የዘምባባ ዘይት መጨመር።
    • ከዚያም ቀላቅሎ ቁስሉን በቀን 3 ጊዜ ማሸት።
    • ንፁህና አዲስ ዝግጅት በየጠዋቱ ማድረግ።

 

ምንጭ      
 (Dr. Theodor Shimmel ፤ Translation:- Teshome Negash )

Advertisement