ፕሮፌሰር ሃይሌ ገሪማን በጨረፍታ

                                      
(የዘመን አቆጣጠሩ ሁሉ እንደ አውሮፓውያን ነው ) 
ከአሥር ልጆች አራተኛ በመሆን የተወለደው ኃይሌ ገሪማ መጋቢት 1946 ላይ ነው ይችን አለም የተቀላቀለው ፡፡ እናቱ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት አስተማሪ ሲሆኑ አባቱ አቶ ገሪማ ተፊካ ደግሞ የተውኔት እና የቴአትር አዘጋጅ ነበሩ፡: እንደ ሳንኮፋ ድረገጽ ከሆነ ፕሮፌሰር ሃይሌ ገሪማ ገና በወጣትነት ዘመኑ የአባቱን ፈለግ በመከተል በአባቱ ቲያትሮች ይለማመድ ነበር ፡፡ ሃይሌ እና እህቱ ዘመናዊ ትምህርት ቤት በመሄድ በቤተሰባቸው ውስጥ የመጀመሪያዎቹ እንደሆኑ ድረገጹ ጠቅሶ የሃገሩን ባህል እና ሥርዓተ ትምህርት በማስተማር እና ለአሜሪካ የሰላም ጓድ አባላት እንዴት ፊደል መጻፍ እንደሚቻል በማስተማር እንዲሁም ባህሉን በማስተዋወቅ የድርሻውን ተወጥቷል ፡፡
ፕሮፌሰር ሃይሌ. "ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ በፈጠራ ጥበብ ማዕከል ውስጥ አጭር ቆይታ ካደረገ በኋላ, ድራማ ለማጥናት ወደ አሜሪካ አቅንቷል፡፡እዚያም ሸሪኪያና ከተባለች ሴት ጋር በትዳር ተጣምሮ አምስት ልጆችን አፍርቷል፡፡
በሎስ አንጀለሰ ከተማ ካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ ከ1976 ጀምሮ የፊልም ጥበብን በማስተማር ስራ ላይ ተሰማርቶ ይገኛል ፡፡
የፊልም ጥበብ ቀማሪው ፕሮፌሰር ሃይሌ ገሪማ ከሰራቸው ፊልሞች መካከል አወር ግላሰ ፣ ቻይልድ ኦፍ ሬንሰንስ ፣ ቡሽ ማማ የተባሉ ስራዎችን በ1975 የሰራ ሲሆን ስሪ ታውዘንድ የተሰኘ ፊልም በ1976 ፣ዊልምግተን ፣ቴን ዩ ኤስ ኤ ቴን ታውዘንድ የተሰኘን ፊልም በ1977 አሽስ ኤንድ ኢምበርስ በ1982 ፣ አፍተር ዊንተር ስተርሊን ብሮውን በ1985 ፣ሳንኮፋ በ1993 አድዋ አን አፍሪካን ቪክትሪ በ2000 የሰራ ሲሆን በዩኒቨርሲቲው ተሸላሚም ነው፡፡ የፓን አፍሪካን የፊልም አዘጋጆች ፌዴሬሽን እና የአፍሪካን የፊልም አዘጋጆች ኮሚቴ አባልም ነው ፕሮፌሰር ሃይሌ ገሪማ፡፡
ከሰራቸው ፊልሞች መካከል:-
• 1972 - Hour Glass Hour Glass
• 1972 - Child of Resistance
• 1976 - Bush Mama
• 1976 - Mirt Sost Shi Amit (also known as Harvest: 3,000 Years)
• 1978 - Wilmington 10 -- U.S.A. 10,000
• 1982 - Ashes and Embers
• 1985 - After Winter: Sterling Brown
• 1993 - Sankofa
• 1994 - Imperfect Journey
• 1999 - Adwa - An African Victory
• 2009 - Teza
Over the course of his career, Gerima has received numerous awards and distinctions in film festivals:-
• 1976 - Grand prize / Silver Leopard for Harvest: 3,000 Years- Locarno
• 1982 - Grand Prix Award for Ashes and Embers-Lisbon International Film Festival
• 1983 - FIPRESCI Film Critics Award for Ashes and Embers-Berlin International Film Festival
• Outstanding Production Ashes and Embers - London Film Festival
• 1984 - Tribute Festival De la Rochelle, France
• 1987 - Long Metrage De Fiction-Prix de la Ville de Alger for Ashes and Embers
• 1993 - Best Cinematography Award for Sankofa, FESPACO, Burkina Faso
• 2003 - Lifetime Achievement Award, 4th Annual Independence Film Festival, Washington D.C.
• 2006 - Festival De Cannes Selection Official Cannes Classic -Harvest: 3,000 Years
• 2008 - Venice Film Festival Special Jury Prize and Best Screen Play Award - Teza
• 2009 - Jury Award at the 18th International Film Festival Innsbruck/Austria - Teza
• 2009 - Golden Stallion of Yennenga at the FESPACO African Film Festival - Teza http://www.rfi.fr/actuen/articles/111/article_3102.asp
• 2009 - Dioraphte Award Hubert Bals film in highest audience regard at the Rotterdam Film Festival
• 2009 - Golden Tanit/Best Film Award for its "modesty and genius," Best Music (Jorga Mesfin Vijay Ayers), Best Cinematography (Mario Massini), Best Screenplay (Haile Gerima), Best Supporting Actor Abeye Tedla at the Carthage/Tunisia Film Festival for Teza
• 2009 - Golden Unicorn and Best Feature Film at the Amiens/France International Film Festival France for Teza
• 2009 -The Human Value's Award at the Thessaloniki Film Festival in Greece for Teza
• 2009 - Official Selection at the Toronto Film Festival for Teza
ፕሮፌሰር ሃይሌ ገሪማ በሚሰራቸው የፊልም ጥበቦች ሃገሩን በማሰተዋወቅ ባለውለታ እንደሆነ ብዙዎች ይመሰክሩለታል፡፡ ወደፊትም በሚያበረክታቸው የፊልም ስራዎቹ ውስጥ ለሃገሩ ልዩ ቦታ እንደሚሰጥ ተናግሯል፡፡
#TEFERI_MIHIRET

Advertisement