የሻዎር ጭንቅላቶች የባክቴሪያ መራቢያ ሊሆኑ ይችላሉ

የሻዎር ጭንቅላቶች የባክቴሪያ መራቢያ ሊሆኑ እንደሚችሉ አንድ ጥናት አመለከተ።

ጥናቱ በአሜሪካ ደቡብ ካሊፎርኒያ ፣ ፍሎሪዳ እና ኒውዮረክ ግዛቶች የተደረገ ሲሆን፥ የሻወር ጭንቅላቶች የባክቴሪያ መራቢያ ሊሆኑ እንደሚችሉ ተረጋግጧል።

የመታጠቢያ ቤቶችን በማጽዳት ሂደት የሻዎር ጭንቅላቶች ትኩረት የማይሰጣቸው ሲሆን፥ ለሳንባ ህመም መንስኤ ነው የተባለው ባክቴሪያ በሻወር ጭንቅላቶች ውስጥ መገኘቱ ተገለጿል።

የመታጠቢያ ቤቶቻችንን ለማጽዳት ጥረት ማድረጉ የተገለመደ ቢሆንም፥ ጽዳቱ ትኩረት የሚደረገው ሲንከሮች እና መቀመጫ ገንዳዎች ላይ ብቻ መሆኑ ተነግሯል።

በዚህም በሻወር ጭንቅላት እና ውሃ መስመሮች ላይ ለጤና ጠቃሚ፣ ጎጅ እና ጎጂ ያልሆኑ ባክቴሪያዎች የተገኙ ሲሆን፥ ከባክቴሪያዎቹ መካከል ለሳንባ ህመም መንስኤ ነው የተባለው ባክቴሪ ዝርያ መገኘቱም ነው የተገለጸው።

እርጥበት ባለበት አካባቢ ሁሉ በቀላሉ ባክቴሪያወች እንደሚራቡ የተገለጸ ሲሆን፥ ከላይ የተጠቀሰው የባክቴሪያ ዘርያ በሻዎር ጭንቅላት ውሰጥ መገኘቱ በቀጥታ ለሳንባ ህመም የማያጋልጥ መሆኑም ተነግሯል።

በሻዎር አዋሳሰዳችን ላይ ለውጥ ማድረግ የሌለብን እና የመታጠቢያ ክፍሎችን ስናጸዳ የሻዎር ጭንቅላቶችን ማጽዳት አንደሚገባ በጥናቱ ተጠቁሟል።

የጤና ችግር እና የሰውነት በሽታን የመከላለከል አቅም ውስንንነት ላለባቸው ሰዎች ግን ቅድመ ጥንቃቄ ለማድረግ ያስችላል ተብሏል።

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement

10 Comments

Comments are closed.