ከጆሮ በስተጀርባ የሚገኝ አጥንት ኢንፌክሽን (Mastoditis)

ከጆሮ በስተጀርባ የሚገኝ አጥንት ህመም በባክቴሪያ አማካኝነት የሚመጣ ነዉ፡፡አብዛኛዉን ጊዜ የመካከለኛዉ እና የዉስጠኛዉ የጆሮ ክፍል ላይ ኢንፌክሽን ሲኖር የሚከሰት ቢሆንም ጤናማ ያልሆኑ የቆዳ ህዋስ ማደግ (Cholesteatomas) ሲኖር እንዲሁም የጆሮ ቱቦ ላይ መዘጋት ሲኖር ሊከሰት ይችላል፡፡ በአግባቡ ካልተከመ እስከ ሞት ሊያደርስ ይችላል፡፡

ይህ ህመም አጣዳፊ (Acute mastoditis) በአብዛኛዉ ህጻናት ላይ የሚከሰት እና ስር የሰደደ(chronic mastoditis) በመባል በሁለት ይከፈላል፡፡

ምልክቶች

 • ከፍተኛ ትኩሳት በተለይ ህመም የተከሰተበት ቦታ ላይ
 • የጆሮ ጫፍ(Ear lobe) እብጠት
 • ከጆሮ በስተጀርባ በኩል እብጠት፣መቅላት ፣መግል እና ህመም
 • ከጆሮ የሚወጣ ጠረን ያለዉ ፈሳሽ
 • ራስ ምታት
 • የመስማት አቅም መዳከም
 • ጆሮ ወደ ፊት መገፋት

ሊደረጉ የሚችሉ ምርመራዎች

 • የነጭ የደም ህዋስ ምርመራ
 • የጆሮ እና ጭንቅላት ኤም አር አይ ምርመራ
 • የጆሮ እና ጭንቅላት ሲቲ ስካን ምርመራ
 • የጭንቅላት ራጅ ምርመራ

ህክምና

 • በባለሙያ እርዳታ መግሉን እንዲፈስ ስና ጆሮ እንዲጸዳ ይደረጋል
 • የጆሮ ጠብታ እና በአፍ የሚወሰዱ መድሐኒቶች ይሰጣል
 • በቀዶ ህክምና እንዲታከም ይደረጋል

በአግባቡ ካልታከመ የሚከሰቱ መዘዞች

 • የፊት መጣመም
 • ተደጋጋሚ ማስመለስ
 • የመስማት ችግር
 • ጭንቅላት እና አከርካሪ አጥንት ላይ መግል
 • የእይታ ችግር
 • ሚዛንን ለመጠበቅ መቸገር
 • የደም መርጋት
 • ማጅራት ገትር በሽታ

ምንጭ: ዶክተር አለ

Advertisement