የጉበት ብግነትን (hepatitis) ሊያመጡ የሚችሉ የቫይረስ አይነቶች

የጉበት ብግነት (hepatitis) ማለት የጉበት ህዋሶች መቆጣት ነው፡፡ ይህን ችግር በአብዛኛው ጊዜ የሚያመጡት ቫይረሶች ናቸው፡፡ ሁሉም የጉበት ብግነትን ሊያመጡ የሚችሉ ቫይረሶች ተላላፊ ናቸው፡፡

የጉበት ብግነትን (hepatitis) ሊያመጡ የሚችሉ ቫይረሶች እና መተላለፊያ መንገዶች

– የጉበት ቫይረስ A ተላላፊ ሲሆን በህመሙ ከተጠቃ ሰው ወደ ጤነኛ ሰው የሚተላለፈም በጉበት ቫይረስ A በተያዘ ሰው ሰገራ ምግብ እና ውሃ ሲበከል ነው በአብዛኛው ጊዜ ህጻናትን ያጠቃል፡፡

 • የጉበት ቫይረስ B ተላላፊ ሲሆን የሚተላለፈውም በቫይረሱ ከተጠቃ ሰው ጋር ያለኮንዶም ግብረስጋ ግኑኝነት በማድረግ እና ስለታማ ነገሮችን በጋራ በመጠቀም ከእናት ወደ ልጅ እና በላብ ሊተላለፍ ይችላል፡፡
 • የጉበት ቫይረስ C ተላላፊ ሲሆን በማንኛውም የሰውነት ፈሳሽ ንክኪ ሊተላለፍ ይችላል፡፡
 • የጉበት ቫይረስ D ብዙውን ጊዜ ህመም ሊያስከትል አይችልም ነገር ግን ከጉበት ቫይረስ B ጋር ሲሆን ህመም ሊያስከትል ይችላል፡፡
 • የጉበት ቫይረስ E ይህ የቫይረስ አይነት ውሃ ወለድ ሲሆን በተበከለ ውሃ ይመጣል፡፡
 • ከላይ የተጠቀሱ ዋና ዋናወቹ ሲሆኑ ሌሎችም የቫይረስ አይነቶች የጉበት ብግነት ሊያመጡ ይችላሉ፡፡
የጉበት ብግነት በሁለት ይከፈላል

-አጣዳፊ የጉበት ብግነት (acute hepatitis) ማለት ከ6 ወር በላይ ያልቆየ የጉበት ብግነት ማለት ነው፡፡ ሁሉም የቫይረስ አይነቶች አጣዳፊ የጉበት ብግነትን ሊያመጡ ይችላሉ፡፡

– የጠና የጉበት ብግነት (chronic hepatitis) ማለት ከ6 ወር በላይ በሰውነት ውስጥ የሚቆይ እና በህክምና መዳን የማይችል ነው፡፡የጠና የጉበት ብግነት (chronic hepatitis) ሊያመጡ የሚችሉ ቫይረሶች የጉበት ቫይረስ B እና የጉበት ቫይረስ C ናቸው፡፡

ከጉበት ቫይረስ B እና ከጉበት ቫይረስ C ውጪ ያሉ ቫይረሶች በራሳቸው የመዳን እድል አላቸው፡፡

ምልክቶች

 • ድካም
 • ጉንፋን የመሰለ ህመም
 • የሽንት መጥቆር (የሽንት መደፍረስ)
 • የሰገራ ቀለም መቀየር
 • የሆድ ህመም
 • የምግብ ፍላጎት መቀነስ
 • ክብደት መቀነስ
 • የአይን እና የቆዳ ቢጫ መሆን

መፍትሄዎች

የህመሙ ምልክቶች ከታዩ ቶሎ ወደ ህክምና ተቋም መሄድ፡፡በህመሙ ከተጠቁ በቤት ውስጥ በ ቫይታሚን C የበለጸጉ ምግቦችን መመገብ እና የተመጣጠኑ ምግቦችን መመገብ፡፡ ከላይ የተጠቀሱ መተላለፊያ መንገዶችን አውቆ መጠንቀቅ፡፡

ምንጭ: ዶክተር አለ

Advertisement