ቲማቲምን ለብጉር

በቀላሉ በምናገኘው ቲማቲም ቡጉርን፤የቆዳ ጥቁረትን እነዲሁም ጥቁት ነጠብጣብን እንዴት ማጥፋት እንደምንችል አዲስ ውህድ ይዘንላችው መተናል፡፡
መዘጋጀት ያለባቸው ነገሮች
1) 1 ቲማቲም
2) 2 የሻይ ማንኪያ ስኳር
3) 2 የሻይ ማንኪያ ማር
4) 1 መለስተኛ የቡና ሲኒ

አዘገጃጀት
1) በመጀመርያ የፊታችን የቆዳችን ቀዳዳዎች መከፋፈት ስላለባቸው ፊታችንን
በሙቅ ውሀ እንፋሎት መታጠን አለብዎ፡፡ 
2) ቲማቲሙን የይቆርጡና በሲኒ ላይ ይጨምቁታል፡፡
3) ጭማቂው ላይ ቅድሚያ ስኳሩን ቀጥሎ ማሩን ይጨምሩና ያዋህዱታል፡፡
4) ቀጥሎ ውህዱን ፊትዎ ላይ በስሱ ይቀቡታል ፡፡
5) ለ 2 ደቂቃ በዝግታ ያሹታል ለተጨማሪ 2 ደቂቃ ደግሞ ባለበት ይተውታል፡፡
6) ባጠቃላይ ከ 4 ደቂቃ በኋላ በ ቀዝቃዛ ውሀ ይታጠቡታል
ይህ ውህድ ለቲማቲም ሆነ ከላይ ለተጠቀሱት ውህዶች አለርጂክ ከሆኑ እንዲጠቀሙት አይመከርም፡፡

መረጃው ለሌሎች የሚጠቅም መስሎ ከተሰማዎ ለሌሎችም ያጋሩልን ፡፡ 
ከጧት 2 ሰዓት እስከ ማታ 2 ሰዓት ከሰኞ እስከ ሰኞ ቢደዉሉ የዶክተር አለ! ሀኪሞች ሊያማክሩዎ በመስመር ላይ ይገኛሉ፡፡

ምንጭ: ዶክተር አለ (Doctor Alle)

Advertisement