የ “ዘመን” ድራማ አዘጋጅ የነበረው ተወዳጁ አርቲስት መስፍን ጌታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

አርቲስት መስፍን ጌታቸው በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል በህክምና ሲረዳ ቆይቶ በኮቪድ-19 ምክንያት በተወለደ በ50 አመቱ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።

አርቲስት መስፍን ጌታቸው በርካታ የጥበብ ስራዎችን በድርሰት፣ በአዘጋጅነት እና በትወና ለአገሩ ያበረከተ ሁለገብ ባለሞያ ነበር።አርቲስቱ በኢትዮጵያ ሬድዮ ዝነኛ የነበረው የቀን ቅኝት ድራማ ደራሲ እንዲሁም በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያገኘው የሰው ለሰው ተከታታይ ድራማ ደራሲ እና ተዋናይ ነበር።አርቲስት መስፍን ጌታቸው የዙምራ ፊልም፣ መንታ መንገድ የሬድዮ ተከታታይ ድራማ እና ሌሎችም ስራዎችን በተለያዩ የቴሌቪዥን እና የሬድዮ ጣቢያዎች ለህዝብ ማድረስ ችሏል።አርቲስት መስፍን ጌታቸው ባለትዳር እና የሶስት ልጆች (የሁለት ሴት እና የወንድ ልጅ) አባት ነበር።

ምንጭ: ኢቢኤስ

May be an image of 1 person and sky

Advertisement