ትራምፕ ከትዊተርና ከፌስቡክ ለሁልጊዜ ታገዱ

ዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎቻቸው የካፒቶል ሂል ግቢን መውረራቸውና አደጋ ማድረሳቸውን ተከትሎ ከዋነኛዎቹ የማኅበራዊ ሚዲያ የትስስር ገጾች ከትዊተርና ከፌስቡክ ታገዱ።

የዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች የታችኛውና የላይኛው ምክር ቤት መሰብሰቢያ የሚገኝበትንና የመንግሥት መቀመጫ የሆነውን ካፒቶል ሒልን ጥሰው በመግባት አደጋ አድርሰዋል። ዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎቻቸውን ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ጠንካራ መልእክት ያስተላልፋሉ ተብሎ በሚጠበቅበት ሰዓት እወዳችኋለሁ የሚል መልእክት ማስተላለፋቸው ተገልጿል።

ትራምፕ የተለመደውን ምርጫው ተጭበርብሯል የሚለውን ያልተጨበጠ ክስም በማኅበራዊ ገጻቸው አስተላልፈዋል።ካፒቶል ሒል የመውረሩ የነውጥ እንቅስቃሴ በዋናነት እነዚህኑ ማኅበራዊ የትስስር መድረኮችን በመጠቀም የተደረገ በመሆኑ እንዲሰረዝ ተደርጓል መባሉን ቢቢሲ ዘግቧል።

አማርኛ ጽሑፍ ምንጭ: ኢቢሲ

Advertisement