የዓይን መንሸዋረር (Strabismus)

ውጫዊ የሆነ ችግር ሲያጋጥም ከስነ አእምሮ ጀምሮ ስጋት ያሳድርብናል ስለሆነም የዓይን መንሸዋረር ምንነት እና ህክምናው ምን እንደሚመስል ይዘን ቀርበናል ተከታተሉን፡፡

  • ሁለቱ ዓይኖች ወደ ተለያየ አቅጣጫ ሲመለከቱና አንዱ ወይም ሁለቱ ዓይን መደበኛ ማዕከላዊ ቦታውን ለቆ ወደ ውጭ ወይም ወደ ውስጥ አለያም ወደ ላይ ወይም ወደ ታች ሲያዘነብል የዓይን መንሸዋረር (ስትራቢዝመስ) ተብሎ ይጠራል፡፡
  • ይህ የዓይን ጤና ችግር በማንኛውም የእድሜ ክልል ሊታይ ቢችልም በብዛት የሚከሰተው ግን በልጆች ላይ ነው፡፡

የዓይን መንሸዋረር ለምን ይከሰታል?

በአይን ጡንቻዎች የሓይል ሚዛን መዛባት ምክንያት ሲሆን በአጠቃላይ በውበት ላይ ከሚያመጣው ተፅዕኖ ባሻገር እይታ እንዲቀንስ ብሎም የህፃናትና የልጆች ዓይን እንዲሰንፍ ሊያደርግ ይችላል፡፡የተወሰኑ ጨቅላ ህፃናት ሲወለዱ የዓይን መንሸዋረር ችግር ሊኖርባቸው ይችላል ፡፡ በተወሰኑት ላይ ደግሞ ከተወለዱ በሗላ ይከሰታል፡፡በጥቅሉ ይህን መሰል ችግር ከሚያስከትሉ የታወቁና ተጠቃሽ መንስኤዎች ጥቂቶቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡

  • በዓይን ጡንቻዎች ላይ የሚደርስ ቀጥተኛ ጉዳት
  • በዓይን ጡንቻዎችን በሚያንቀሳቅሱ ነርቮች ላይ የሚደርስ ጉዳት (ችግር)
  • በዓይን ጡንቻዎችን በሚመግቡ የደም ሥሮች ላይ የሚደርስ ጉዳት (ችግር)
  • በዓይን በተፈጥሮ እና በሌሎች ምክንያቶች የሚደርስ የሓይል መዛባት ችግር በሌሎች የዓይን ጤና ችግሮች (ለምሳሌ፡- በመነፅር ሊስተካከል የሚችል የእይታ ችግር፣የዓይን ካንሰር፣ ወዘተ.)ኩፍኝ ፣ ከጭንቅላት ፈሳሽ መብዛት ጋር ተያይዞ የሚመጣ የራስ ቅል መተለቅ ፣ የስኳር ህመም ፣ መርዛማ የእንቅርት ችግር ፣ የጭንቅላት ደም መፍሰስ በጭንቅላት ላይ የሚደርስ የምት አደጋ እንዲሁም አንዳንድ የዓይን ቀዶ ህክምናዎች በጡንቻዎች ፣ በነርቮች ወይም የደም ስሮች ላይ ጉዳት ሊያስከትሉ ስለሚችሉ ለዓይን መንሸዋረር ችግር መንስኤ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

ህክምና

የሚደረገው ህክምና እንደ ችግሩ መንስኤና ደረጃ የሚለያይ ቢሆንም ዋና ዋና የህክምና አይነቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡

  • የመነፅር ህክምና
  • የዓይን አካል ብቃት እንቅስቃሴ
  • የዓይን መንሸዋረር ቀዶ ህክምና

ምንጭ: ዶክተር አለ

Advertisement