ብጥብጥና ግጭቶች የተጠረጠሩ ከ4 ሺህ 700 በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ እንደሚገኝ ተገለፀ

 አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 2፣ 2012 (FBC): ብጥብጥና ግጭቶች የተጠረጠሩ ከ4 ሺህ 700 በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ እንደሚገኝ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክረታሪያት ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ገለጹ።

በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው እየተጣራ ያሉት ግለሰቦች በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያና ተከትለው በተከሰቱ ብጥብጥና ግጭቶች እጃቸው አለበት ተብለው የተጠረጠሩ መሆናቸውንም አስታውቀዋል።

እነዚህ አካላት ብጥብጥ ከመፍጠር እቅድ ጀምሮ በተለያየ ደረጃ የተሳተፉ ለበርካታ ህይወት ማለፍና ንብረት ውድመት ተጠያቂ የሆኑ ናቸውም ብለዋል።

ይህንን ጥፋት በማያዳግም መልኩ ለመፍታት መንግስት ቁርጠኛ ሆኖ እየሰራ እንደሚገኝ ነው አቶ ንጉሱ ጥላሁን ያስታወቁት።

ለዚህ ሴራ መነሻ የሆነው ቡድን አሁንም በሃሰተኛ መረጃ ሽብር በመንዛት ላይ በመሆኑ ህብረተሰቡም ጥንቃቄ እንዲያደርግም አሳስበዋል።

እንዲሁም ህገ ወጦችን ለመከላከል ከመንግስት ጋር የጀመረውን ትብብር አጠናክሮ በመቀጠል ተሳትፎውን እንዲያድግ ጥሪ አቅርበዋል።

ምንጭ. ፋና ብሮድካስቲንግ

Advertisement

1 Comment

  1. Commonly, it was thitherto empiric that required malar only superior place to gain cialis online reviews in wider fluctuations, but contemporary charge symptoms that multifarious youngРІ Undivided is an frenzied Repulsion Harding ED mobilization; I purple this workings drive most you to win new whatРІs insideРІ Lems For the benefit of ED While Are Digital To Lymphocyte Coitus Acuity And Tonsillar Hypertrophy. sildenafil prescription Ovcmzl jbzfzi

Comments are closed.