ህፃናት ዘመናዊ ስልኮች ላይ ረጅም ጊዜ እንዲያሳልፉ ማድረግ በዕድገታቸው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል

ህፃናት በዘመዊ ስልኮች ላይ ረዘም ያለ ጊዜ እንዲያሳልፉ መፍቀድ በእድገታቸው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር አንድ ጥናት አመላከተ።

በካናዳና አሜሪካ ባለሙያዎች የተካሄደው ጥናት እንደሚያሳየው ህፃናት በዘመናዊ ስልኮች፣ ቴሌቪዥን፣ ኮምፒዩተርና መሰል የቴክኖሎጅ ውጤቶች ላይ ብዙ ጊዜ እንዲያሳልፉ ማድረግ በሚኖራቸው የዕድገት ሁኔታ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል።

በጥናቱ ብዙ ጊዜያቸውን በእነዚህ የቴክኖሎጅ ውጤቶች ላይ የሚያሳልፉ ህፃናት የቋንቋ አጠቃቀም ችሎታቸው ዝቅተኛና አዝጋሚ እንደሚሆንም በጥናቱ ተመላክቷል።

ይህም ህፃናቶቹ ከቤተሰቦቻቸውና ከማህበረሰቡ ጋር ያላቸውን ግንኙነት በመቀነስ በማህበራዊ ህይዎት ላይ ያላቸውን የተግባቦት ሁኔታ ይገድባል ተብሏል።

ከዚህ ባለፈም ህፃናቱ የሚሰማቸውን ስሜት እንዳይገልጹ በማድረግ በቀጣይ የሚኖራቸውን የራስ መተማመን ችሎታ ይቀንሳልም ነው የሚለው የጥናቱ ውጤት።

በተጨማሪም ህፃናቱ የተለያዩ አካላዊ እንቅስቃሴዎችን በተገቢው ጊዜና ሰዓት እንዳይለማመዱ የሚያደርግ መሆኑም ነው የተገለፀው።

ስለሆነም ወላጆች ዕድሜያቸው ከ18 በ ወራት በታች የሆኑ ህፃናትን ምንም አይነት ሞባይልም ሆነ ሌሎች የቴክኖሎሎጅ ውጤቶችን እንዲጠቀሙ መፍቀድ የለባቸውም ተብሏል።

ከ18 እስከ 24 ወራት እድሜ ያላቸውን ህጻናት ደግሞ የተመረጡና ጠቃሚ የሆኑ ፕሮግራሞችን ብቻ ለአጭር ጊዜ እንዲመለከቱ መፍቀድ አስፈላጊ መሆኑም በጥናቱ ተመላክቷል።

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.