ካሮትና አቮካዶን ጨምሮ ለአይናችን ጤና እና የእይታ ጥራት የሚረዱ ምግቦች

ለዓይን ጥራት ከፍተኛ ጥቅም አለው በሚል ለምግብነት ከሚውሉት ውስጥ ካሮት ቀዳሚውን ስፍራ እንደሚይዝ ብዙዎቻችን እናውቃለን።

ተመራማሪዎች ከሰሞኑ ባወጡት የጥናት ውጤት ደግሞ ከካሮት በተጨማሪ አትክትሎችን ጨምሮ በርካታ ምግቦች የአይናችንን የእይታ ጥራት እና ጤና ለመጠበቅ ጠቀሜታ አላቸው ብለዋል።

የዓይንን ጤንነት እና የእይታ ጥራት ለመጠበቅ የሚረዱ ምግቦችም፦

  1. አቮካዶ

አቮካዶ ሉተን እና ዠያንቲን የተባሉ አንቲ ኦክሲደንት ንጥረ ነገሮችን በውስጡ የያዘ በመሆኑ በብርሃን ምክንያት በዓይናችን ላይ የሚደርሰውን ጉዳት የመከላከል አቅሙ ከፍ ያለ ነው ተብሏል።

በፈረንሳይ የተሰራ ጥናት እንዳመለከተው፥ ዠያንቲን የተባለው አንቲ ኦክሲደንት በዕድሜ ምክንያት የሚከሰት የእይታ ችግር፣ በደም ግፊት፣ ለከፍተኛ የብርሃን ጨረር በመጋለጥ እና በአመጋገብ ችግር በዓይናችን ላይ የሚከሰተውን የጤና ችግር ይከላከላል።

በተጨማሪም አቮካዶ ቫይታሚን ሲ በውስጡ በመያዙ አይናችን ጤነኛ ሆኖ አንዲቆይ እንደሚረዳም ነው ጥናቱ ያመለከተው።

  1. እንቁላል

እንቁላል የዓይናችንን ጤና በመጠበቅ በኩል ያለው ጠቀሜታም ከፍተኛ መሆኑ ይነገርለታል።

የቫይታሚን ኤ ምንጭ የሆነው እንቁላል ለዓይን ጤንነት ጠቃሚ ነው የተባለ ሲሆን፥ ልክ አንደ አቮካዶ የእንቁላል አስኳልም ዠያንቲን የተባለው አንቲ ኦክሲደንት በውስጡ በመያዙ በብርሃን ጨረር ምክንያት በዓይን ላይ የሚከሰትን ጉዳት ለመከላከል ይረዳል።

  1. ካሮት

ካሮት የዓይናችንን የእይታ ጥራት እንደሚጨምር ከዚህ በፊት ሲነገር የነበረ ሲሆን ፥ በዚህኛው ጥናት ማረጋገጫ ማግኘቱም ተነግሯል።

በቫይታሚን ኤ የበለፀገው ካሮት ቤታ ካሮቲን የተባለ ንጥረ ነገር በውስጡ በመያዙ የዓይናችን የእይታ ጥራት ከፍ ያለ እንዲሆን እንደሚያደርገው ጥናቱ አመልክቷል።

በጥናቱ ላይ እንደተመለከተው ቫይታሚን ኤ፣ ቤታ ካሮቲን፣ ቫይታሚን ሲ፣ ቫይታሚን ኤ፣ ዚንክ እና ኮፐር ንጥረ ነገሮችን የሚወስዱ ሰዎች ከአድሜ ጋር ተያይዞ ለሚከሰት የዓይን ችግር የመጋለጥ እድላቸው 25 በመቶ  የቀነሰ መሆኑ ተረጋግጧል።

  1. አረንጓዴ ሻይ

አረንጓዴ ሻይ በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች እንዳሉት የሚነገርነት ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ የሰውነትን ክብደት ለመቀነስና የአእምሮን የመስራት አቅም መጨመር ተጠቃሽ ሲሆኑ፥ ከዚህ በተጨማሪም ለዓይናችን ጤንነት ጠቃሚ መሆኑ ተነግሯል።

በአረንጓዴ ሻይ ውስጥ ያሉት እንደ ቫይታሚን ሲ፣ ሉተን እና ዠያንቲን የተባሉ አንቲ ኦክሲደንቶች ካንሰርን፣ የልብ ህመምን እና የዓይን በሽታን ለመከላከል እንደሚረዱ ጥናቱ አመልክቷል።

ከዚህ በተጨማሪም በአረንጓዴ ሻይ ውስጥ የሚገኘው ገሎካትቺን የተባለ ንጥረ ነገር ለዓይን ጤንነት ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑንም ነው ጥናቱ ያመለከተው።

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement

15 Comments

  1. I used to be recommended this web site by way of my cousin. I’m now not certain whether this put up
    is written via him as nobody else recognize such specific about my trouble.
    You are amazing! Thank you!

  2. You’re so interesting! I do not believe I have read
    through anything like this before. So nice to discover somebody with some unique thoughts on this subject.

    Seriously.. thanks for starting this up. This site is something that’s needed on the internet, someone with
    a little originality! yynxznuh cheap flights

  3. naturally like your web-site however you need to test the
    spelling on several of your posts. Many of them are rife with spelling problems and I in finding it very troublesome to tell the
    reality nevertheless I will definitely come again again.

Comments are closed.