የቴክኖሎጅ ኩባንያዎች የአውስትራሊያ ፓሊስ ስማርት ስልኮችን መከታተል የሚያስችለውን ህግ ተቃወሙ

በአውስትራሊያ መንግስት የዋትስ አፕና አይ ሜሴጅ አገልግሎት ተጠቃሚዎች  የግል ጉዳይን መከታተል የሚያስችለውን አሰራር ህጋዊ ማድረጉን ተከትሎ ፌስቡክና ሌሎች የቴክኖሎጅ ኩባንያዎች ስጋት እንደገባቸው አስታወቁ፡፡

መንግስት አዲሱ ህግ ፓሊስና የፀጥታ ተቋማት ሽብርተኝነትንና በህፃናት ላይ የሚደርስ ፆታዊ ጥቃትን ለመከላከል የሚያስችል መሆኑን አስታውቋል፡፡

ሆኖም የቴክኖሎጅ ኩባንያዎችና ሲቪል ማህበራት ውሳኔው ከፋ ባለደረጃ በቢዝነሱ እና በተጠሚዎቻቸው ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እንደሚኖረው ነው የተናገሩት፡፡

ውሳኔው በዋትስ አፕ፣ ጎግል እና አፕልን በመሳሰሉ የቴክኖሎጅ ኩባንያዎች ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እንደሚኖረው የፌስቡክ ቃል አቀባይ ቤን ማክኮናጋይ ተናግረዋል።

እንዲሁም መተግበሪያውን በሚጠቀሙ ሰዎች ላይ ስጋትን እንደሚፈጥር የተገለፀ ሲሆን፥ ኩባንያዎችም በአውስትራሊያ በዘርፉ እንዳይሰማሩ ሊያደርግ ይችላል ተብሏል፡፡

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.