ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትነት ሆነው ተሾሙ

በሙለታ መንገሻ

ወይዘሮ መአዛ አሸናፊ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትነት ሆነው ተሾሙ።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው እለት ባካሄደው ስብሰባው በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በእጩነት የቀረቡትን ወይዘሮ መአዛ አሸናፊ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትነት አድርጎ ሾሟል።

ምክር ቤቱም ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትነት በእጩነት የቀረቡትን ወይዘሮ መአዛ አሸናፊን ሹመት በሙሉ ድምጽ ነው ያፀደቀው።

ወይዘሮ መአዛ አሸናፊም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አቶ ሰለሞን አረዳን ለጠቅላይ ፈርድቤት ምክትል ፕሬዚዳንት እጩነት አቅርበውም አፀደቀዋል።

ምክር ቤቱም አቶ ሰለሞን አረዳ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው እንዲሾሙ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።

አቶ ሰለሞን አረዳም በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

 

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.