በአፍ ፋንታ አየርን በአፍንጫ መሳብ እና ማስገባት የማስታዎስ አቅምን ይጨምራል

በአፍ ፋንታ አየርን በአፍንጫ መሳብ እና ማስገባት የማስታዎስ አቅምን እንደሚጨምር አንድ ጥናት አመላክቷል።

በዚህም ማዕዛዎችን የመለየት እና የመረዳቱ ተግባር ነገሮችን ከመልመድ እና ከማስታዎስ ጋር እንደሚያያይዝም ነው በጥናቱ የተገለጸው።

ለዚህም የማስታዎስ አቅምን ለማሻሻል አየርን በአፍ ከመሳብ እና ከማስወጣት ይልቅ በአፍንጫ መለማመዱ ጠቃሚ ነው ተብሏል።

የቤተ ሙከራ አይጦች አየር የሚስቡት በአፋቸው ሳይሆን፥ በአፍንጫቸው መሆኑ ነው በዘገባው የተመላከተው።

ይህንን ሀሳብ መነሻ በማድረግም በስዊድን የካሮሊንስካ ኢኒስቲቲዩት ተመራማሪዎች  ሁለት ቡድኖችን   12 ንጥረ ነገሮችን በሁለት መንገዶች እንዲለዩ በማድረግ በአፍ ፋንታ አየርን በአፍንጫ መሳብ እና ማስወጣት የማስታዎስ አቅምን እንደሚጨምር አረጋግጠዋል።

በዚህም በጥናቱ የተካተቱ  ሰዎች ንጥረ ቅሞችን እንዲሁ በማየት እና አየር በአፋቸው በመሳብ እና በማስወጣት ንጥረ ነገሮቸን እንዲያጠኑ ሲያደርጉ በሌላ በኩል ደግሞ አየር በአፍንጫቸው በማሳብ እና በማስወጣት ንጥረ ቅመሞቹን እንዲያጠኑ ማድረጋቸው ተገልጿል።

በመጨረሻም አየር በአፍንጫቸው በመሳብና በማስገባት ንጥረ ነገሮችን ያጠኑት  ቡድን አባላት በአንጻሩ አየር በአፋቸው እየሳቡና እያስወጡ እንዲያጠኑ ከተደረጉት ቡድን አባላት በተሻለ ደረጃ ንጥረ ነገሮችን ለመለየት እና ለመረዳት መቻላቸው ነው የተገለጸው።

በጥናቱ የተካተቱ ሰዎች አየር በሰርንአቸው ሲያስወጡና ሲያስገቡ ከሚረዱት ማዕዛ በተጨማሪ በዚሁ በኩል የሚያልፈው አየር ለአዕምሮ ስሜት እንደሚሰጥ ነው በጥናቱ የተጠቆመው።

ይሁን እንጂ በጉዳዩ ላይ ሰፊ እና ጥልቅ ምርምሮች መደረግ እንዳለባቸው ነው ዘገባው የሚያስረዳው።

ምንጭ: ቢቢሲ

Advertisement

2 Comments

Comments are closed.