በጎግል ፕሌይ ስቶር ላይ ሚገኙ መተግበሪያዎች 90 በመቶዎቹ የግለሰቦችን መረጃ ያለፍቃድ እየወሰዱ ነው ተባለ

በሞባይል መተግበሪያዎች አማካኝነት የግለሰቦችን መረጃ ያለፍቃድ የመሰብሰብ እና ለሌሎች የማካፈል ስራ ከቁጥጥር ውጭ እየሆነ መምጣቱን በኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የተሰራ ጥናት አመልክቷል።

በጥናቱ ከጎግል ፕሌይ ስቶር ላይ በነፃ ከሚገኙ መተግበሪያዎች 90 በመቶዎቹ የግለሰቦችን መረጃ ያለፍቃድ እየወሰዱ ለጎግል እህት ኩባንያ ለሆኑት አልፋቤት እንደሚያቀብሉም ተገልጿል።

ከሚወሰዱት መረጃዎች ውስጥም እድሜ፣ ጾታ፣ አድራሻ እና አጠቃላይ የግል መረጃዎችን ጨምሮ በስማርት ስልኩ ላይ ምን አይነት መተግበሪያዎች አሉ የሚሉት ተጠቃሽ ናቸው።

ከግለሰቦች የሚወሰዱት መረጃዎችም ለተለያዩ አገልግሎቶች ይውላሉ የተባለ ሲሆን፥ ከእነዚህም ውስጥ ማስታወቂያዎችን ማሰራጨት እና በኢንተርኔት ለሚደረጉ የምርጫ ቅስቀሳዎች ጥቅም ላይ እንደሚውሉ ተጠቅሷል።

ኩባንያው በዚህ መልኩ የግለሰቦችንን መረጃ ያለፍቃድ እየሰበሰበ ገቢውን እያሳደገ ነው የተባለ ሲሆን፥ በአሜሪካ ብቻ የጎግል አመታዊ ገቢ 59 ቢሊየን ዶላር መድረሱን ነው ጥናቱ ያመለከተው።

ጎግል በበኩሉ ጥናቱ በመተግበሪያዎ ላይ ያቀረበው መረጃ ትክክል አለመሆኑን በመጥቀስ፤ ጎግል በዚህ ዙሪያ ግልጽ ፖሊሲ እንዳለው አስታውቋል።

በጎግል ፕሌይ ላይ በነፃ የሚለቀቁ መተግበሪያዎች የኩባንያውን ፖሊሲ የሚጥሱ ከሆንም እርምጃ ይወሰድባቸዋል ነው ያለው ጎግል ኩባንያ በሰጠው ምላሽ።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.