ጥርት ያለ የፊት ቆዳ ለማግኘት

Barrinton Russell

የፊት ቆዳችንን በአግባቡ ካልተንከባከብነው በቀላሉ የሚጎዳ ሲሆን ቀጥሎ ያሉትን የፊት ቆዳን መንከባከቢያ መንገዶች ይመልከቱ።

– ፊትን በቀን ሁለቴ መታጠብ
– የፊት ሳሙና ወይም ሌላ ቅባት ሲቀቡ የፊትዎን ቆዳ ከመፈተግ ይቆጠቡ ይልቁንም በለስላሳና ክባዊ እንቅስቃሴ ቀስ ብለው ይቀቡት
– ለፊት ቆዳዎት የሚስማማ ማርጠቢያ ክሬሞችን ይጠቀሙ ከመተኛትዎትም በፊት ሊጠቀሙት ይችላሉ
– የፊት ቆዳ ቀዳዳን ከሚደፍኑ ዘይታማ ከሆኑ ሜክአፖችና የቆዳ ክሬሞች ይራቁ
– የቆዳችን ንፅህና መጠበቅ በተለይ ብጉር የሚያስቸግረን ከሆነ ቤንዞይል ፐርኦክሳይድ፣ ፊዞርሲኖል፣ ሳሊክሊክ አሲድ ወይም ሰልፈር ያለው ለፊትዎ የሚስማማ ሳሙና መጠቀም ብጉሩ በዚህ ካልቀነሰ ሀኪም ማማከር ያስፈልጋል

በቤት ውስጥ የሚዘጋጅ መድሃኒት

በተለያየ ምክንያት የፊትና ሌላ የቆዳ አካል ላይ የቀረን ምልክትን ለማጥፋት ከፈለጉ የሚከተለውን በቤት ውስጥ የሚዘጋጅ ህክምናን ሊጠቀሙ ይችላሉ።

መድሃኒቱን በቤት ውስጥ ለማዘጋጀት፦

• አራት የሻይ ማንኪያ የሎሚ ጁስ
• አራት የሻይ ማንኪያ ማር
• አንድ አስኳሉ የወጣለት እንቁላል

አዘገጃጀት

• ፊትዎ/ቆዳዎ ንፁህና ደረቅ መሆን ስላለበት ይታጠቡት
• በመቀጠልም ከላይ የተዘረዘሩትን በንፁህ እቃ ውስጥ በደንብ ያደባልቁ
• ከዚያም ምልክት ባለበት የቆዳዎ ክፍል ላይ ይቀቡት
• ከ15 ደቂቃ ቆይታ በኋላ ይታጠቡት

ጥሩ ውጤት ለማግኘት በሳምንት ሁለት ጊዜ እንዲጠቀሙት ይመከራል።

ምንጭ: ዶክተር አለ(Doctor Alle)

Advertisement

3 Comments

  1. The Working Aggregation Carrying-on Of which requires offensive cervical to a not many that develops patients and RD, wood and worldwide fettle, and then reaches an important differential of profitРІitРІs blue ribbon hold up at 21 it. canadian sildenafil Puewwa hfvusc

Comments are closed.