ስለ “ጳጉሜ” ምን እናውቃለን? (ለጠቅላላ ዕውቀት) | What Do We Know About The Ethiopian Intercalary Month “Pagume”

Advedrtisment

“ጳጉሜ” የወር ስም ሆኖ በነሐሴ እና በመስከረም ወራት መኻል የሚገኝ ከአስራ ሦስቱ ኢትዮጵያ የወራት አቆጣጠር ውስጥ የመጨረሻው እና አሥራ ሦስተኛው (፲፫ ኛው) የወር ስም ነው። «ጳጉሜ» በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር ዘመነ ዮሐንስ ሥግር ዓመት (በጎርጎርያዊአቆጣጠር leap year) በመሆኑ ስድስት (፮) ዕለታት አሉት። በዘመነ ልቆስ፣ ዘመነ ማቴዎስ እና በዘመነ ማርቆስ አምስት (፭) ዕለታት አሉት።

“ጳጉሜ” የሚለው ስም ምንጩ ከግሪክ ቋንቋ ሲሆን “ቀሪ ዕለታት” ማለት ነው። ነሐሴ የክረምት ሦስተኛው ወር ነው።

ኢትዮጵያ በአለም ብቸኛዋ የ13 ወራት ጸጋ ባለቤት ናት። ይህ የጳጉሜን ወር በኢትዮጵያውያን ዘንድ የምህረት ወር ተብሎ ይታመናል። ወደ አዲስ አመት መግቢያ (መሸጋገርያ) ወርም ነው።

ምንጭ: Wikipedia

3 Comments

  1. እንኳን ለ2011ዓም አዲስ አመት አደረሳችሁ።
    መረጃው የተሟላ ቢሆን አሪፍ ይሆናል።

  2. ጳጉሜን 6 የምትሆነው በዘመነ ሉቃስ መጨረሻ ላይ ነው። 6 መሆኗ የሚታወቀው ዓመቱ ለ4 ተካፍሎ ቀሪው 3 ከሆነ ያ ዓመት 6 ይሆናል። ዘንድሮ 2011 ቀሪው 3 ስለሆነ ሉቃስ ነው። ጳጉሜንም 6 ሆና ዓመቱን ትፈጽማለች። በወንጌላውያን ቅደም ተከተል መሠረትም 3ኛ ሉቃስ ነው። 1 ማቴዎስ 2 ማርቆስ 3 ሉቃስ 4 ዮሐንስ። “ሠግረ ዮሐንስ፣ መባሏም ዮሐንስ ተራምዶ የሚውልባት ስለሆነ ነው። ጎበዝ በዊኪፒዲያ ላይ ሙሉ እምነት አታሳድሩ። ይዘባርቃልና።

    • ሁሌም ስለዚህች ወር ሲጠቀስ ግር የሚለው ጉዳይ ስም አጠራሯ ይመስለኛል። ዛሬ ዛሬ ላይ ባመዛኙ፣ ለዚህ ፅሁፍም ርዕስ እንደተደረገው “ን” ትገደፋለች። አንዳንዶች “ቋቅሜ፣ ቋቅሚት፣ ጳግሚት” ሲሉም ይደመጣል። ሌሎችም ሌላ ሌላ። ስለቃሉ አመጣጥ፣ ትክክለኛ አጠራር እና ትርጓሜ ባለቤት የሆነችውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያንን ጎራ ብሎ ማወያየቱ ሳይጠቅም አይቀርም። ወንድሜ ሄኖክ የሰጠው አስተያየትም፣ ስያሜውን አስተካክሎ (ጳጉሜን) ማስቀመጡ ጭምር፣ ማለፊያ ነው ። እስቲ በነካ እጃችሁ ጅምሩን ምሉዕ ለማድረግ መላ በሉ።

Leave a Reply

Your email address will not be published.


*