NEWS: ባህሬን ለኳታር ዜጎች የቪዛ አገልግሎት መስጠት አቆመች

ባህሬን ለኳታር ዜጎች የቪዛ አገልግሎት መስጠት እንዳቋረጠች አስታወቀች፡፡

ከዓመት በፊት አራት የአረብ ሀገራት ሳዑዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች፣ ባህሬንና ግብጽ ሙሉ ለሙሉ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን ማቋረጣቸው ይታወሳል፡፡

ሆኖም ኳታር እስከአሁን ድረስ የቪዛ አገልግሎቱን በይፋ ማቋረጧን አላስታወቀችም ነበር ተብሏል፡፡

አሁን ተግባራዊ የሆነው የቪዛ እገዳ በባህሬን የሚማሩ የኳታር ዜግነት ያላቸው ተማሪዎችን አይመለከታቸውም ተብሏል፡፡

የሀገሪቱ ባለስልጣናት ይህንን እርምጃ የወሰዱት ኳታር የጎረቤት ሀገራትን ጥቅም በተጻረረ መልኩ በወሰደችው ኃላፊነት በጎደለው ተግባሯ ነው ይላሉ፡፡

ሁለቱ ሀገራት በተደጋጋሚ የውሃ አካላትንና የአየር ክልል በመጣስ በሚል ሲካሰሱ ቆይተዋል፡፡

ባህሬን እና ወዳጆቿ ኳታር ከሙስሊም ወንድማማቾችና ከኢራን ጋር ያላትን የጠበቀ ግንኙነት በተደጋጋሚ ሲኮንኑት ይታያል፡፡

እንዲሁም በአካባቢው ሀገራት የውስጥ ጉዳይ ላይ ጣልቃ መግባቷንም እንድታቆም እንፈልጋለን ሲሉ ይደመጣሉ፡፡

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.