NEWS: «ኦነግ ሀገር ለመገንጠል ነው የምሠራው ብሎ አያውቅም» ሽጉጥ ገለታ (ዶ/ር)

ግማሽ ምዕተ ዓመት የደፈነውን የ “ኦሮሞ ነጻነት ግንባር” ፍኖተ-ትግል የሚገልጹ ሁለት ቁልፍ ቃላት ብናስስ “ጠረጴዛ” እና “ጠመንጃ”ን እናገኛለን።

“ጠረጴዛ” ግንባሩ የአሮሞ ሕዝብን ጥቅም እና ፍላጎት ለማሳካት ያደረጋቸውን ሰላማዊ የድርድር አፍታዎች ይወክላል።

“በ1991 የሽግግር ዘመን ወቅት ተሳትፈን ነበር።የሰላም እና ዲሞክራሲ በር የተከፈተ መስሎን…፣ኾኖም በ1992 ሀገር ዓቀፍ ምርጫ ወቅት ኢህአዴግ ያሳየውን [ያልተገባ ሁኔታ] ተከትሎ ወደ ትጥቅ ትግል ለመግባት ተገደናል” ሲሉ የድርጅቱ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ሽጉጥ ገለታ (ዶ/ር) ያስታውሳሉ።

“ጠመንጃ”ው ደግሞ በጠረጴዛ ዙሪያ የጠየቃቸው ጥያቄዎች ባለመሟላታቸው ከበርሀ እስከ ጫካ ሲፋለም የከረመባቸውን ዓመታት ይጠቁማል።

• ”በደኖ የሚባል ቦታን ረግጨው አላውቅም” አቶ ሌንጮ ለታ

• ከምዕራብ ኦሮሚያ ከተሞች ጥቃት ጀርባ ያለው ማን ነው?

ከባሌ ጫካ እስከ ኢትዮ-ኬንያ ድንበር ከዚያም አልፎ እስከ ኤርትራ በርሃ የሚዘረጉ የደም መፋሰስ ዘመናትን ያስታውሳል። ኦነግ ከሰሞኑ ዳግም ወደ ‘ጠረጴዛው’ መጥቷል።

“መንግሥት አሳማኝ ጥረት እያደረገ መስሎ ስለታየን፤ ለትጥቅ ትግል የሚገፋፉትን ነገሮች ወደኋላ ትተን ወደ ሀገር ቤት ለመግባት ወስነናል።” የሚሉት የድርጅቱ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ “በሕዝቡ መሐል ሆነን ለሰላም፣ዲሞክራሲ እና ፍትህ የምናደርገው ትግል ጠቀሜታ ያለው ስለመሰለን[ከዚህ ውሳኔ] ደርሰናል።” ይላሉ።

ይህን የተናገሩት ከሰሞኑ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዚደንት አቶ ለማ መገርሳ ወደ አስመራ በማቅናት እዚያ መሽገው ከከረሙት የኦነግ መሪ ዳውድ ኢብሳ ጋር ያደረጉትን ስምምነት ተከትሎ ስለተላላፈው ድርጅታዊ ውሳኔ ሲያስረዱ ነው።

ኦነግ የመገንጠል ጥያቄን ትቷል?

የአሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር ለዓመታት ካራመዳቸው አቋሞቹ መካከል አንዱ «የሕዝቦች የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት እስከ መገንጠል» የሚለው እና በኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 39(1) ላይ የተጠቀሰው ሐሳብ «እንዲተገበር» መጠየቁ ነው።

ጥቂት የማይባሉ የፖለቲካው ዓለም ሰዎች አንቀጹን ኢትዮጵያን ለመበታተን የተቀመጠ ሕግ አድርገው የሚቆጥሩትን ያክል ኦነግን ደግሞ አንቀጹን ተጠቅሞ ከኢትዮጵያ የተገነጠለች ‘ኦሮሚያ’ የተባለች ሀገር ለመመሥረት ሊጠቀምበት እንዳቆበቆበ ቡድን አድርገው ይቆጥሩታል።

ለዚህም ነው ኦነግ ወደ ሀገር ቤት ሊመለስ መሆኑ በተሰማ ማግስት ከተሰሙ ጥያቄዎች ሁሉ «ኦነግ የሚታወቅበት የመገንጠል አቋም ላይ ለውጥ አድርጎ ይሆን?» የሚለው ጎልቶ የወጣው።

ዶ/ር ሽጉጥ ገለታ በዚህ ጉዳይ ላይ በሁለት የሚከፈሉ መልስ አሏቸው።መልሶቻቸው ራስን በራስ ከማስተዳደር እና ከመገንጠል ፅንሰ ሐሳብ የሚመነጩ ይመስላሉ።

እሳቸው እንደሚሉት ሕዝቦች እራሳቸውን በራሳቸው እንዲያስተዳድሩ ፣የግለሰብ እና የሕዝብ መብቶች ተጣጥመው እንዲከበሩ የሚጠይቀው የድርጅታቸው አቋም ላይ “ከበፊቱ የተለወጠም ሆነ አዲስ የተጨመረ” አቋም የለም።

• ፓርላማው የኦነግ፣ ኦብነግና ግንቦት 7 የሽብርተኝነት ፍረጃ መነሳትን አፀደቀ

• ”ኦነግ በሚቀጥሉት ቀናት ወደ አገር ቤት ይገባል”

ኦሮሚያን ከኢትዮጵያ ግዛት ገንጥሎ በማስተዳደር ጉዳይ ለሚነሱ ጥያቄዎች የድርጅቱ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ መልሳቸውን የሚጀምሩት ጥያቄው በተሳሳተ መንገድ በድርጅቱ ላይ የተለጠፈ መሆኑን በመጥቀስ ነው።

“የድርጅቱን ጥያቄ የመገንጠል፣የዘረኝነት፣የአክራሪነት ጥያቄ ነው [እየተባለ]የሚወረወሩበት [ውንጀላዎች] አሉ። ኦነግ በታሪኩ ውስጥ በኢትዮጵያ ውስጥ ከነበሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች እራሱን ገለልተኛ አድርጎ ለሀገር መገንጠል ነው የምሠራው ብሎ በግልፅ የተናገረበት ጊዜ የለም።” ሲሉ ያስረግጣሉ።

“ከኢትዮጵያ ምሥረታ ጀምሮ የኦሮሞ ሕዝብ የተያዘው በኃይል ነው።” በማለት የሚሞግቱት ኃላፊው ቀጥለው የመጡ አገዛዞች የሕዝቦችን ፍላጎት እና ስሜት ለማክበር አለመፍቀዳቸው የችግሮች መነሻ ኾኖ መቆየቱን ያነሳሉ።

ድርጅታቸው ለዚህ መፍትሄ የሚሆነውን፣ ሕዝቦች በመብታቸው ላይ ለመወሰን ያላቸውን ልዑላዊነት እንዲከበር መታገል፣ባሻቸው አስተዳደራዊ ብሂል እና ቋንቋ ካለ ከልካይ እንዲጠቀሙ መሟገትን በመሰሉ የመብት ጥያቄዎች ላይ መሥራትን ወደፊትም እንደሚገፋበት ያሰምሩበታል።

የኦነግ ጦር ዕጣ ፋንታ

ከ1983 ዓ. ም የሥርዓት ለውጥ በኋላ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሠራዊት ካላቸው ተፋላሚዎች መካከል አንዱ ኦነግ እንደነበር ይነገራል።

ይሄ ጦር በተለያየ ጊዜያት በተቃጣበት ጥቃት እና በአስተናገዳቸው የድርጅቱ መሰንጠቅ ሰበብ ቁጥሩ በዓመታት ውስጥ ቢቀንስም አሁንም በኤርትራ በርሃዎች የሚንቀሳቀስ ታጣቂ ክንፍ አለው።

ኦነግ ወደ ሰላማዊ ትግል ሊመለስ ስምም ማድረጉን ተከትሎ የዚህ ጦር ዕጣስ ምን ይሆናል የሚል ጥያቄ መነሳቱ አልቀረም።

የድርጅቱ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ዶ/ር ሽጉጥ የሠራዊቱ አባላት እንዴት ወደ ሰላማዊ ሕይወታቸው እንደሚመለሱ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ስምምነት ላይ እንደደረሰና ዝርዝሩም በቅርቡ ይፋ እንደሚሆን ፍንጭ ሰጥተዋል።

የኦነግ ነገ፡ ጠረጴዛ ወይስ ጠመንጃ?

በአዲሱ ኢትዮጵያ መንግሥት እና ኦነግ ስምምነት መሠረት ድርጅቱ መርሃ ግብሮችን ለሕዝብ እንዲያስተዋውቅ ፣ፖለቲካዊ እንቅስቃሴዎች እንዲያደርግ እንደተፈቀደለት ዶ/ር ሽጉጥ ይጠቅሳሉ።

በዚህም መሠረት በህቡዕ ድርጅቱን ሲያገለግሉ የነበሩ ወገኖች ወደ አዲሱ ሰለማዊ ትግል በይፋ ይጠራሉ።የድርጅቱ ሊቀመንበር እና ከፍተኛ አመራሮች ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳሉ።

ድርጅቱ ከሌሎች ፖለቲካ ድርጅቶች ጋር በመሆን በወንድማማችነት ዑደቱን ይቀጥላል።

ምንጭ: ቢቢሲ

 

Advertisement

39 Comments

  1. According OTC lymphatic procedure derangements РІ here are some of the symptoms suggestive on that end result : Gyves Up Now Equally Outstanding Command Associated Ache Duro Rehab Thickening-25 Fibrous Beat Can Merely Revealed Mr. sildenafil online generic Eakeih pbzxnw

  2. Antimicrobial dislike reduced and contagious agents such as hypertension, tachycardia, hypertension, diagnostic or peaked right side up being treated in african to one or more careful criticism a. canada sildenafil Eymyre etkfsd

Comments are closed.