NEWS: እንግሊዝ ፌስቲቫል ተሳታፊ የአፍሪካ ፀሐፊዎችን ቪዛ ከለከለች

በብዙ የሚቆጠሩ አፍሪካውያንና የመካከለኛው ምስራቅ ፀሐፊዎች በስኮትላንድ የሚዘጋጀውን የመፅሐፍ ፌስቲቫል ለመሳተፍ ቪዛ ባለማግኘታቸው አለመሳተፋቸውን አዘጋጆቹ ገልፀዋል።

“ሁኔታው በስርአቱ የሚደገፍና ጥልቀት ያለው ነው። ” በማለት የኤዲንበርግ አለም አቀፍ መፅሐፍ ፌስቲቫል ዳይሬክተር ኒክ ባርሌይ በማለት ለጋርዲያን ጋዜጣ ተናግረዋል።

“ይህ በጣም አደገኛ የሆነ አካሄድ ነው። ቪዛ የጠየቁትን ፀኃፊዎች ምንም አይነት ጥያቄ ሳያቀርቡላቸው ነው ውድቅ ያደረጉት” በማለት አክለው ተናግረዋል።

ክረምትና ንባብ

“ህልም አለኝ”:-በቀለ ገርባ

“የኢትዮጵያ የህክምና ታሪክ አልተጠናም” ዶክተር አሰፋ ባልቻ

በባለፈው ወር እንዲሁ በታዋቂው ወማድ የሚል መጠሪያ ባለው ወማድ ፌስቲቫል በዕቅድ ተይዘው ከነበሩት ሶስት የአፍሪካውያን የጥበብ ስራዎች በቪዛ ችግር ምክንያት ስራቸውን ሳያቀርቡ ቀርተዋል።

ይህንንም ሁኔታ በመታዘብ “የነጮች ስብሰባን ብቻ ነው የምንፈልገው? ሌላውን አለም የማትቀበል ሀገር ነው የምንፈልገው?” በማለት የወማድ መስራች ፒተር ገብርኤል ይጠይቃሉ።

ምንጭ: ቢቢሲ

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.