NEWS: ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የ D.F.I.D ሃላፊ የሆኑት ፔይኒ ሞርዳንትን ዛሬ በፅ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ፡፡

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ከእንግሊዝ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት (ዲ ኤፍ አይ ዲ) ዋና ፀሃፊ ፔኒ ሞርዳውንት ጋር ተወያዩ።ውይይታቸውን በኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች እና ድህነት ቅነሳ ላይ አድርገው መክረዋል።..

ዋና ፀሃፊዋ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን ለውጥ አድንቀው፥ ዲ ኤፍ አይ ዲ
ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ያለውን ትብብር እንደሚያጠናክርም ገልፀዋል።

ዋና ፀሃፊዋ በዛሬው እለት በድርጅቱ ድጋፍ የኢትዮጵያን የግብር አሰባሰብ ስርዓት ለማሻሻል የሚያግዝ የ35 ሚሊየን ፓውንድ ፕሮግራም ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በኢትዮጵያ እያደረጉ ባለው ጉብኝት በሃዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ በመገኘት፥ የሚመሩት ድርጅት የሰራተኞችን ዋስትና እና ደህንነት ለመጠበቅ ያደረገውን የ3 ሚሊየን ፓውንድ ድጋፍም ይፋ አድርገዋል።

ከዚህ ባለፈም በድርጅቱ ለቀጣዮቹ ስድስት አመታት የሚተገበረውንና በ80 ሚሊየን ፓውንድ የተቸገሩ ኢትዮጵያውያን እና ስደተኞችን ለማገዝ የተጀመረውን የስራ እድል ፈጠራ ፕሮግራምም ጎብኝተዋል።

የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ክብር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ የእንግሊዝ ዓለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ድ

ርጅት (ዲ.ኤፍ.አይ.ዲ) ሃላፊ የሆኑት ፔይኒ ሞርዳንትን ዛሬ በፅ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ፡፡

የውይይቱ ማጠንጠኛ በኢኮኖሚ እና በድህነት ቅነሳ ዙርያ ላይ ያደረገ ነው፡፡

ፔይኒ ሞርዳንት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚካሄደው ለውጥን አድንቀው የሚመሩት ድርጅት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ያለውን ትብብር እንደሚያጠናክር ገልፀዋል፡፡
ምንጭ:- የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት

ምንጭ: ኢቢሲ

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.