የነፍሰጡር እናቶች በቂና ተመጣጣኝ እንቅልፍ ማግኘት ለጽንስ ጤና አስፈላጊ ነው

የነፍሰጡር እናቶች በቂና ተመጣጣኝ እንቅልፍ ማግኘት ለጽንስ ጤና አስፈላጊ መሆኑን አንድ ጥናት አመለከተ።

የደቡብ አውስትራሊያ ተመራማሪዎች እንደገለጹት የነፍሰ ጡር እናቶች በቂና ተማጣጣኝ እንቅልፍ ማግኘት ጽንስ መወለድ ባለበት ጊዜ እንዲወለድ በማድረግና የጽንስ መቋረጥን በመከላከል ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ ነው።

የእናቶች በእርግዝና ጊዚያቸው በቂ አንቅልፍ ማግኘት ጽንሱ መወለድ ካለበት ጊዜ ቀድሞ እንዳይወለድ ያደረግጋል ተብሏል።

በጥናቱ አዋቂዎች የህይወታቸውን አንድ ሶስተኛ ያህል በአንቅልፍ የሚያሳልፉ ሲሆን፥ በተመሳሳይ መልኩ ጽንስም ከእርግዝና ጊዜ አንድ ሶስተኛ ያህሉን ጊዜ በእንቅልፍ እንደሚያሳልፍ ነው የተገለጸው።

በዚህም የነፍሰ ጡር እናቶች በቂና ተመጣጣኝ እንቅልፍ ከጽንሱ ጤና ጋር ተያያዥነት ያለው ሲሆን፥ ነፍሰ ጡር እናቶች በጀርባቸው መተኛት እንደሌለባቸው ተመላክቷል።

ነፍሰጡር እናቶች በጀርባቸው ሲተኙ የጽንሱ የኦክስጅንና የምግብ ተደራሽነት እንደሚቀንስ ነው በጥናቱ የተጠቆመው።

እናቶች በቂ እንቅልፍ የማያገኙና ለእንቅልፍ ችግሮች የተጋለጡ ከሆኑ ጽንሱ መወለድ ካለበት ቀን ቀድሞ የመወለድ እድሉ ከፍ እንደሚል በዘገባው ተመለክቷል።

ጥናቱ መወለድ ከላባቸው ጊዜ ቀድመው በመወለድ አደጋ የሚደርስባቸውን ህፃናት ቁጥር ለመቀነስ የሚደረገውን ጥረት በማገዝና የጽንስ ጤና እንክብካቤ ከፍ ለማድረግ አንደሚያስችል ነው ዘገባው የሚያስረዳው።

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.