NEWS: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ሁለት ፓትሪያርክ ይኖራታል

ከሃያ ዓመታት በላይ ተለያይተው የነበሩት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን የሀገር ቤትና የውጭ ሲኖዶሶች ተዋህደው አብረው ለመስራት ተስማሙ።

በትናንትናው ዕለት አሜሪካ ውስጥ ሲኖዶሶቹ በሰጡት መግለጫ ቤተ-ክርስቲያኗ ወደቀደመ ክብሯና አንድነቷ እንድትመለስ የነበረው ችግር በውይይት እንዲፈታ መወሰናቸውን ተከትሎ ከሁለቱ ሲኖዶሶች የተወከሉ አባቶች ጉዳዩን በጥልቀት እንደተነጋገሩበት ተገልጿል።

• የመደመር ጉዞ ወደ አሜሪካ

• የኦርቶዶክስ ቤተ-ክርስትያን ከክፍፍል ወደ ውህደት

በማጠቃለያውም ሲኖዶሶቹም ስለደረሱበት ውሳኔ የጋራ መግለጫ አውጥተዋል። በዚህም መሰረት የ1983ቱን የመንግሥት ለውጥ ተከትሎ ለስደት የተዳረጉት አቡነ መርቆርዮስ በፓትርያርክነት ክብርና ደረጃ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

በመንበረ ፓትርያርኩ ግቢ ውስጥም የመኖሪያ ቦታ እንዲዘጋጅላቸውም ወስነዋል። የሥራ ክፍፍላቸውንና አፈፃፀምን በተመለከተ ፀሎትና ቡራኬ በማድረግ ቤተ-ክርስቲያኗን እንዲያገለግሉ በሚልም ተስማምተዋል።

አቡነ ማትያስም በቤተ-ክርስቲያኗ ህግ መሰረት የአስተዳደር ሥራውን እየሰሩ እንዲቀጥሉና በፀሎትና ቡራኬም ሃላፊነታቸውን እንደሚወጡ በመግለጫው ተካቷል።

• ደቡብ ሱዳን ለመኪና መግዣ 16 ሚሊየን ዶላር አወጣች

• የቅኔው ተማሪ በአሁኑ ዘመን

• የኢትዮጵያ ገና ለምን ታህሳስ 29 ይከበራል?

ከዚህም በተጨማሪ ሁለቱ ፓትርያርኮች በህይወት እስካሉ ድረስ ቤተ-ክርስቲያኗ በእኩልነት እንድትይዛቸውና እንድታያቸው እንዲሁም የሃገር ቤትና የውጪ ሲኖዶሶች የሚለው ስም ቀርቶ አንዲት ቤተ-ክርስቲያን የሚል ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

ምንጭ: ቢቢሲ

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.