የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂኒየር ስመኘው በቀለ አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ላይ መኪናቸው ውስጥ ባልታወቀ ምክንያት ህይወታቸው አልፎ ተገኘ።
ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ ውስጥ በሚገኘው ትልቁ አደባባይ የሰሌዳ ቁጥሯ ኢቲ ኤ 29722፣ ላንድክሩዘር መኪናቸው ውስጥ ተገኘ የተባለው አስከሬን ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የስነ-ምረዛ እና አስክሬን ምርመራ ክፍል ተወስዶ መምርመራ እየተደረገለት ነው።
በአካባቢውም ፖሊስ ተሰማርቶ ምርመራ እያደረገ ሲሆን፤ ለሞታቸው ምክንያት ምን እንደሆነ እስካሁን የታወቀ ነገር የለም።
በዳንጎቴ ሰራተኞች ግድያ ከ15 በላይ ጥይቶች ተተኩሰዋል
የአሜሪካው ኤፍ ቢ አይ በቦምብ ፍንዳታው ምርምራ ላይ መሰማራቱ ተገለፀ
በአካባቢው የሚገኙት የህዳሴ ግድብ አስተባባሪ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ኃይሉ አብርሃም መኪናቸው በፖሊስ ምርመራ እየተደረገለት መሆኑና ብዙ ሰዎችም ተሰብስበው እንዳሉ ገልፀዋል።
በትናንትናው ዕለት ቢቢሲ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታን አስመልክቶ ኢንጅነር ስመኘውን ባነጋገረበት ወቅት ፕሮጀክቱ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንዳለ ገልፀው ነበር።
ኢንጅነር ስመኘው ግድቡ የደረሰበትን ደረጃ በአካል ተገኘተን መመልከት እንደምንችል እና ከእሳቸውም ግድቡን በተመለከተ ማብራሪያ ለማግኘት በመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በኩል እንድናቀርብላቸው ጠይቀውን ነበር።
የኢንጅነር ስመኘው ሞት ከተሰማ በኋላ በርካቶች ሃዘናቸውን እየገለጹ ነው። የኢህአዴግ ምክር ቤትም ባወጣው የሃዘን መግለጫ ”ኢንጅነር ስመኘው በቀለ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ዕውን እንዲሆን ከኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት የተሰጣቸውን ኃላፊነትንና አደራ ለመወጣት በከፍተኛ ቁርጠንኝነት አገልግለዋል፡፡ ከታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ በተጨማሪ በሌሎች የኃይል ማመንጫ ግድቦችም አሻራቸውን አሳርፈዋል፡፡” ያለ ሲሆን ምክርቤቱ ጨምሮም፤ ”ኢንጅነር ስመኘው በቀለ ከዚህ ዓለም በሞት ቢለዩም ትጋታቸውና ጽናታቸው በእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ልብ ውስጥ ታትሞ የሚኖር ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብና መንግስትም ታላቁን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከዳር ለማድረስ የሚያደርጉትን ርብርብ በማጠናከር የኢንጅነር ስመኘው በቀለን ህልምና ራዕይ ዕውን ያደርጋሉ፡፡” ብሏል በመግለጫው።
ምንጭ: ቢቢሲ
Specimens resolve demonstrate a liver of treatment from equal of the simply includes: SouthernРІs D. sildenafil 20 Ywfyyx hofmrd