የታላቁ ህዳሴ ግድብ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ አሟሟት እስካሁን ምን እናውቃለን?

ዛሬ ጠዋት የታላቁ የታላቁ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ አዲስ አበባ መስቀል አደባባይ ላይ መኪናቸው ውስጥ ህይወታቸው አልፎ ከተገኘ በኋላ እሰካሁን ያገኘናቸው አስር የተረጋገጡ መረጃዎች።

• ኢንጂነር ስመኘው በቀለ ህይወታቸው ያለፈው በጥይት ተመተው ነው፡ ፌደራል ፖሊስ

•የህዳሴው ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ስመኘው በቀለ በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ መኪናቸው ውስጥ እንዳሉ ሞተው ተገኙ።

•ኢንጅነር ስመኘው ሞተው የተገኙት በሹፌር መቀመጫ ላይ እንዳሉ ነበር። ኢንጅነር ስመኘው ቀይ ጃኬት ለብሰው፤ ኮፍያ አድርገው የነበረ ሲሆን ጭንቅላታቸው ወደ ቀኝ ዘንበል ብሎ ነበር።

•ኢንጅነር ስመኘው ሞተው የተገኙባት መኪና ላንድ ክሩዘር ቪ8 ስትሆን የሰሌዳ ቁጥሯም ኮድ 3 ኢቲ ኤ29722 ነው።

•በቦታው የነበረው የቢቢሲ ጋዜጠኛ እንደተመለከተው አስክሬናቸ የተገኘበት መኪና ፊቷን ወደ ኢስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን አዙራ በአግባቡ ነበር የቆመችው። የዓይን እማኞች ጨምረው እንደተናገሩት የመኪናው ሞተር ለረጅም ሰዓት አልጠፋም ነበር።

•በስተቀኝ በኩል ያለው የመኪናዋ የኋላ መቀመጫ ትንሿ መስኮት ተሰብሮ ይታያል። ነገር ግን መኪናው ተቆልፎ ስለነበር ለመክፈት በፖሊሶች እንደተሰበረ ታውቋል።

•ከረፋዱ 5፡40 ላይ አስክሬናቸው ለምርመራ ወደ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የሥነ-ምረዛና የአስክሬን ምርመራ ክፍል ተወስዷል።

•የፖሊስ አባላት ኢንጅነር ስመኘው የነበሩበትን መኪና እያሽከረከሩ ይዘዋት ሄደዋል።

•አስክሬኑም ሆነ መኪናዋ ከቦታው ላይ እንዲነሱ ከተደረገ በኋላ የቢቢሲ ጋዜጠኛ በቦታው ላይ የደም ጠብታዎችን እና ፖሊስ በምርመራው ወቅት የተጠቀመበትን የእጅ ጓንቶች ተመልክቷል።

•የኢንጅነሩን ሞት ተከትሎ የተቆጡ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ህንጻ ፊት ለፊት በመገኘት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።

•የፌደራል ፖሊስ ጄነራል ዳይሬክተር ዘይኑ ጀማል ከኢንጂነሩ አስከሬን ጎን ሽጉጥ መገኘቱንና በጥይት መሞታቸውን ተናግረዋል።

ምንጭ: ቢቢሲ

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.