NEWS: በሞሪታኒያ የቀድሞዋ ባሪያ ለሕዝብ እንደራሴነት ልትወዳደር ነው

በ2008 ከተሸጠችበት ባርነት ነፃ የወጣችው ሞሪታኒያዊቷ በመስከረም ወር ሊካሄድ ቀጠሮ በተያዘለት የሕዝብ እንደራሴነት ልትወዳደር መሆኑን በሀገሪቱ የሚገኘው የፀረ ባርነት ቡድን አስታወቀ።

ሐቢ ሚንት ራባህ በሐገሪቱ ቅንጅት ከፈጠሩ የፖለቲካ ማህበሮች ለአንዱ ነው የምትወዳደረው።

“በ 5ዓመቴ ነበር ባሪያ የሆንኩት። በየዕለቱ ከብቶች እጠብቅ ነበር። በየዕለቱ በአሳዳሪዬ እደፈር ነበር” ስትል ተናግራለች ከባርነት ነፃ ከወጣችበኋላ።

• ኳታር ለመጀመሪያ ጊዜ የመነሻ ደሞዝ መጠንን ይፋ አደረገች

• የወባ መድሃኒት ጥቅም ላይ ሊውል ነው

• በአዲስ አበባ የሚኖሩ የጎባ ተወላጆች ከኦሮሚያ ባለሥልጣናት ጋር ተወያዩ

“ምን እንደተፈጠረ ስላልተረዳሁ እየሆነ ያለው ነገር ሁሉ ትክክል ይመስለኝ ነበር”

እንደ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ከሆነ ባርነት በሞሪታኒያ በህግ የተከለከለ ቢሆንም አሁንም ተስፋፍቶ ይገኛል።

የተወሰኑ ብሄር አባላት የሆኑ ጥቁር ህዝቦች ትንሽ ቀላ ያለ መልክ ባላቸው ሞሪታኒያውያን በቤት ሰራተኝነት ባሪያ ተደርገው ይገዛሉ።

ሐቢ ሚንት ራባህ ከባርነት ነፃ የሆነችው በወንድሟ አማካኝነት ነው። ወንድሟ ቢላል ኦልድ ራባህ ራሱን ከባርነት ነፃ ካደረገ በኋላ ለሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ጉዳዩን አሳወቀ።

ለ35 ዓመት በባርነት ካገለገለችበት ነፃ የሆነችውም በእነዚህ የመብት ተሟጋቾች ብርቱ እንቅስቃሴ ነበር።

” እርሷ የባርነት ተጠቂ ናት። አሁን ተቀላቅላናለች እናም በመጪው ምርጫ ባርነትን ደግፈው የሚከራከሩትን ተቃውማ በሕዝብ እንደራሴነት ትመረጣለች” ሲሉ የ አይ አር ኤ ፕሬዝዳንት ቢራም ዳህ አቤድ ተናግረዋል።

ምንጭ: ቢቢሲ

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.