NEWS: ከ60 ዓመት በኋላ የወባ መድሃኒት ጥቅም ላይ እንዲውል ይሁንታ አገኘ

ከ 60 ዓመት በኋላ ወባን ለማከም የሚረዳ ኪኒን በአሜሪካ ባለስልጣናት ፈቃድ አገኘ። መድሃኒቱ በየአመቱ 8 ሚሊየን ሰዎች ላይ የሚያገረሸውን የወባ አይነት ለማከም የሚረዳ ነው።

ይህ አይነት የወባ በሽታ በጉበት ውስጥ ለረጅም ዓመት ተደብቆ የመቆየት ባህሪ አለው። ተመራማሪዎች ይህንን “ድንቅ ስኬት ሲሉ አሞካሽተውታል”።

በአለም ዙሪያ የሚገኙ አስፈፃሚዎች አሁን መድኃኒቱን ለዜጎቻቸው ማዘዝ ይችሉ አይችሉ እንደሆን ይመለከቱታል።

ደጋግሞ የሚያገረሽ የወባ በሽታ ፕላስሞዲየም ቪቫክስ በሚሰኝ ጥገኛ ተዋህሲያን የሚከሰት ሲሆን በአፍሪካ በዋናነት ከሚጠቀሱ የበሽታ አይነቶች መካከል አንዱ ነው።

• የወባ በሽታን በትንፋሽ ማወቅ ተቻለ

• አደገኛ የተባለ የወባ በሽታ በበርካታ ሀገራት ስጋት ፈጥሯል። በኢትዮጵያስ?

• የወባ ትንኝ አደገኛ የሆነችው በሂደት ነው

በወባ ትንኝ አንዴ መነደፍ ብቻ ለህመሙ የሚያጋልጥ ሲሆን በተለይ ህፃናት ይበልጥ ተጠቂ ናቸው። በዚህም የተነሳ ባመማቸው ቁጥር አቅማቸው ከእለት በዕለት እየቀነሰ የሚሄድ ሲሆን ከትምህርት ገበታቸውም ላይ ለመቅረት ይገደዳሉ።

በበሽታው የተጠቁ ሰዎች ባመማቸው ቁጥር የወባ ትንኟ ጥገኛ ተዋስህያኑን ከእነርሱ ወደሌሎች በማዛመት እነሱን መነሻ ታደርጋቸዋለች።

ይህም በሽታውን ከምድረገፅ ለማጥፋት አስቸጋሪ አድርጎታል።

አሁን የአሜሪካው የምግብና የመድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ታፌኖኪውይን ለተሰኘው መድሃኒት እውቅና ሰጥቷል።

መድሃኒቱ በሽታዋ ከተደበቀበችበት ጉበት አውጥቶ በመግደል ሰዎች በህመሙ ዳግመኛ እንዳይሰቃዩ ያደርጋል።

መድሃኒቱ ተጓዳኝ ህመሞችን ለማከም ከሚያግዙ ሌሎች መድሃኒቶች ጋር የሚሰጥ ይሆናል።

በአሁን ሰዓት ጉበት ውስጥ የተደበቀች ወባን ለማከም የሚረዳ ፕሪማኪውን የተሰኘ መድሃኒት አለ።

ነገር ግን አንድ ታፌንኪውንን ወስዶ ከሚገኘው ፈውስ ጋር ሲነፃፀር ፕሪማኪውንን ለ 14 ቀን መውሰድ ይጠይቃል።

• በሀሰተኛ መድሃኒት ሰዎች እየሞቱ ነው

አንዳንድ ባለሙያዎች ግን ሰዎች ይህንን መድሃኒት መውሰድ ከጀመሩ በጥቂት ቀናት ውስጥ ለውጥ በማየታቸው ብቻ አቋርጠውት ዳግመኛ እንዳያገረሽባቸው ይሰጋሉ።

የአሜሪካው የምግብና የመድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን መድሃኒቱ በአሜሪካ ውስጥ ጥቅም ላየ እንዲውል የፈቀደ ሲሆን መታወቅ ያለባቸው የጎንዮሽ ጉዳቶች እንዳሉትም አልሸሸገም።

ምንጭ: ቢቢሲ

Advertisement

4 Comments

Comments are closed.