Eritrean Capital Asmara Through The Eyes of a BBC Journalist | የኤርትራ ዋና ከተማ አሥመራ በቢቢሲ ዘጋቢ አይን

የአሥመራ ነዋሪዎች ከእንግዳ ጋር ሰላምታ ሲለዋወጡ እጅን ከመጨበጥ ይልቅ ማቀፍን ይመርጣሉ። እንግዳው የአስር ሺህዎች ነብስ በበላ መሪር ጦርነት ማግስት ለሃያ ዓመታት ያህል ተኮራርፈው የነበሩት ኤርትራ እና ኢትዮጵያ ሰላም ማውረዳቸውን ተከትሎ ከአዲስ አበባ የመጣ ተጓዥ መሆኑን ሲያውቁ ደግሞ እቅፉን ያጠብቃሉ፣ ፈገግታ ያዘንባሉ፣ ሰላምታው ዘለግ ይላል፣ የደስታ መግለጫ ይግተለተላል።

ለዓመታት ተነጣጥለው የኖሩ ቤተሰቦች፣ ዘመዳሞችና ወዳጆች ዳግመኛ ሲገናኙ መመልከት ልብን የሚነካውን ያህል፤ የማይተዋወቁ ተቃቅፈው ሰላም ሲባባሉ ሲወረገረጉ ማየት ጥያቄን ያጭራል። የጋርዮሽ ታሪክ፣ የባህል፣ የቋንቋ እና የሥነ-ልቦና ፈርጆች ያሰናሰሏቸው እነዚህ ሕዝቦች እንደምን እንዲህ ለረዘመ ጊዜ መቀራረብ ተሳናቸው?ባልተጠበቀ ፍጥነት ያልተለመደ ቀረቤታ መመስረት የቻሉት የሁለቱ አገራት መሪዎች ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ እና ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ እነዚህን የልዩነት ዓመታት “የባከኑ ጊዜያት” ብለው ሲገልጿቸው ተደምጠዋል። መሪዎቹ ከሁለቱ አገራት ግንኙነት ጋር በተያያዘ የአዲስ ምዕራፍ መከፈትን ብስራት ሲያውጁ፤ በዚያውም እነዚህን የባከኑ ጊዜያት ለማካካስ ቃል ገብተዋል።አዲሱ ምዕራፍ በጊዜ ሒደት ምን ዓይነት ይዘት እና ቅርፅ እንደሚኖረው ጥርት ብሎ እንዳልገባቸው የሚገልፁ የአሥመራ ነዋሪዎች አልጠፉም። በክፍለ አህጉሩ፣ ከዚያም አልፎ በአህጉሩ በፖለቲካ እና በምጣኔ ሃብት አቅሟ እየደረጀች ያለችው ኢትዮጵያ የአንድ ወቅት አካሏን መልሳ ትውጥ ይሆን የሚል ስጋት በስሱም ቢሆን መኖሩ አልቀረም።ምናልባትም ይህንን ብዙም ያልተነገረ ስጋት ለማርከስ አስበው፤ አሊያም የሁለቱን አገሮች የዳግም ግንኙነት ዳዴ ከወዲሁ በግልፅ መስፈሪያዎች ለማስቀመጥ ፈልገው፤ የአገሪቱ የማስታወቂያ ሚኒስትር የማነ ገብረ መስቀል የእርስ በእርስ መከባበር እንዲሁም ግዛታዊ ሉዓላዊነት የኢትዮ-ኤርትራ አዲስ ወዳጅነት ውሃ ልክ መሆናቸውን ደጋግመው እና አስረግጠው ይናገራሉ።

በአሥመራ ጎዳናዎች ላይ ወጣት ወንዶችን በብዛት መመልከት ያዳግታልImage copyrightBBC/KALKIDAN
አጭር የምስል መግለጫበአሥመራ ጎዳናዎች ላይ ወጣት ወንዶችን በብዛት መመልከት ያዳግታል

የአዛውንቶች ከተማለበርካታ ዓመታት ኤርትራን “የአፍሪካዋ ሰሜን ኮርያ” እያሉ በአሉታ መግለፅ የተለመደ ሆኖ ቆይቷል። የማያኮራ የሰብዓዊ መብቶች አያያዝ፣ የተቃውሞ ድምፆች አፈና፣ የመንግሥት አድራጊ ፈጣሪነት እና ለተቀረው ዓለም ራሷን ዘግታ የመነነች አገር ተደርጋ መቆጠሯ ነው ለንፅፅሩ መነሾ የሆነው።ባለስልጣናቷ ለትችቶቹም ሆነ ለአገሪቷን የዓመታት መናኒነት እምብዛም ዕውቅና ሲሰጡት ባይስተዋልም፤ በኤርትራ ላይ ከየአቅጣጫው ተደቅነው ቆይተዋል የሚሏቸው የህልውና ስጋቶች ቅድሚያ የሚሰጧቸው ጉዳዮች ላይ ጫና ማሳረፋቸውን ይጠቅሳሉ።

• የኤርትራና የኢትዮጵያ መጪው ፈተና

• ”የኤርትራ ኢኮኖሚያዊ ዕቅድ የተነደፈው በኢትዮጵያ ሃብት ላይ ነበር” አምባሳደር አውዓሎም ወልዱእንዲያም ሆኖ ባለፉት ዓመታት የአገሪቱ መንግሥት ብሔራዊ ኩራትን በህዝቡ ዘንድ ለማስረፅ በርትቶ ሲሰራ መባጀቱን መገመት አያዳግትም። “ኤርትራዊ ነኝ፤ ኩሩ ነኝ” የሚሉ ማስታወቂያዎች በመንግሥት መስሪያ ቤቶች ተለጥፈው ይታያሉ። የአገር ፍቅር መንፈስን የማስረፁ አንዱ አስፈላጊነት አገሪቱ ከምታካሂደው የብሔራዊ ውትድርና አገልግሎት ጋር የሚገናኝበት ክር ይኖርም ይሆናል።ሆኖም ከማዕቀብ፣ ከዓለም መገለል እና ከተደጋጋሚ ግጭቶች ጋር በተገናኘ የኤርትራ ምጣኔ ሃብት ክፉኛ መደቆሱ ይሄንን ብሄራዊ ኩራት ለልምሻ ሳያጋልጠው አልቀረም። በአሥመራ ጎዳናዎች ላይ ወጣት ወንዶችን በብዛት መመልከት ያዳግታል። ሴቶች፣ ታዳጊዎች እና አዛውንቶች በርክተው ይታያሉ። ይህንን ትዝብታችንን ያጋራናቸው ሁለት የከተማዋ ነዋሪዎች ጉዳዩን ከስደት ጋር አያይዘውታል።በየዓመቱ በርካታ ቁጥር ያላቸው ኤርትራዊያን ወጣቶች (ከመካከላቸውም አያሌዎቹ ወንዶች ናቸው) ድህነትን፣ ውትድርና እና አፈናን ሸሽተው ወደአውሮፓ መሰደዳቸው ይዘገባል።በአገሪቱ የስልጣን መዋቅሮች የሚገኙ ኃላፊዎችም በብዛት ኤርትራ ራሷን የቻለች አገር ከሆነችበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን በመንበራቸው ወይንም በተመሳሳይ የኃላፊነት ቦታዎች የቆዩ ሆነው ይስተዋላሉ።በከተማዋ ያለውን የንግድ እንቅስቃሴ የተሟሟቀ ነው ማለት የሚያስቸግር ሲሆን፤ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ ያደረጉ ወጣቶች በቂ የሥራ አማራጭ አለ ብለው እንደማያምኑ ነግረውናል።

የሁለቱ መሪዎች ምስል በየቦታው ይታያልImage copyrightBBC/KALKIDAN

ኢንተርኔት እና ስልክ በአሥመራ ከተማ የገመድ አልባ ድረ-ገፅ አቅርቦት ያላቸው ሆቴሎች እና የኢንተርኔት ካፌዎች ቢኖሩም የአገልግሎታቸው ጥራት እና ፍጥነት የሚያመረቃ አይደለም። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ450 በላይ መንገደኞችን ይዞ የመጀመሪያ ጉዞውን ወደአሥመራ ባደረገበት ዕለት በርካታ ተጓዦች የኢንተርኔት ግልጋሎትን ለማግኘት ወዲያ ወዲህ ሲባትሉ ታዘበናል።

• ኤርትራ የሐይማኖት እሥረኞችን ፈታች

• የንግድ ሽርክና ከኤርትራ ጋር?የከተማዋ የአገልግሎት ዘርፍ ከፍ ያለ ቁጥር ያላቸው እንግዶችን በአንድ ጊዜ የማስተናገድ አቅም ያዳበረ አይመስልም።የተንቀሳቃሽ ስልክን መጠቀም የሚሻ እንግዳ ሲም ካርድ በአፋጣኝ ማግኘት የማይቻለው ሲሆን፤ በከተማዋ ልዩ ልዩ ስፍራዎች ባሉ እና በካርድ በሚሰሩ የህዝብ ስልክ ሳጥኖች መደዋወል በርካቶች የሚመርጡት የመገናኛ ስልት ነው።

የሁለቱን መሪዎች ምስል ከሚሸጡ ታዳጊዎች አንዱImage copyrightBBC/KALKIDAN
አጭር የምስል መግለጫየሁለቱን መሪዎች ምስል ከሚሸጡ ታዳጊዎች አንዱ

ፍቅረ-ብይጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ምናልባትም በቅርብ ጊዜ አሥመራን መጎብኘታቸውን ተከትሎ በከተማዋ ከፍተኛ ተወዳጅነት ሳያተርፉ አልቀሩም።በአደባባዮች ላይ ህፃናት ምስሎቻቸውን የያዙ አልባሳትን እንዲሁም ተለጣፊ ጌጦችን ይሸጣሉ፤ ሱቆች፣ የሽያጭ መደብሮች እንዲሁም የምሽት ክበቦች የእርሳቸውን እና የፕሬዚዳንት ኢሳያስን ፎቶዎች ለጥፈው ይታያሉ።

• ወደ አሥመራ ለመጓዝ ማወቅ የሚገባዎ 6 ነጥቦች

ከዚህም ባሻገር ስለጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚናገሩ በተለያዩ የዕድሜ ክልል የሚገኙ ነዋሪዎች፤ አድናቆታቸውን ገልፀው የሚጠግቡ አይመስልም።ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚመሯት ኢትዮጵያ ባለፉት ሦስት ወራት የተመዘገበውን ዓይነት ፈጣን ለውጥ በአገራቸው ማየት ይፈልጉ እንደሆነ የጠየቅናቸው ነዋሪዎች በተቆጠበ ቋንቋ የለውጥ ተስፋቸውን አጋርተውናል።በሳምንቱ አጋማሽ ኤርትራ ከሃይማኖት ጋር በተያያዘ እስር ላይ የቆዩ ከሰላሳ በላይ እስረኞችን የለቀቀች ሲሆን ይህ እርምጃ በሌሎች የለውጥ እንቅስቃሴዎች ይታጀብ እንደሆነ ገና ግልፅ አይደለም።

በአሥመራ ካሉ የምሽት ቤቶች አንዱImage copyrightBBC/KALKIDAN
አጭር የምስል መግለጫበአሥመራ ካሉ የምሽት ቤቶች አንዱ

አማርኛ በአመራኤርትራ እና ኢትዮጵያ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸውን በይፋ ዳግም ከመጀመራቸው፣ በአካል ተነጣጥለው የቆዩ ቤተሰቦችም ዳግም ከመገናኘታቸው በፊት በሁለቱ አገራት ህዝቦች መካከል ተዘርግቶ የቆየ ኪነ-ጥበባዊ ድልድይ የነበረ ይመስላል።በጥሩ ይዞታ ላይ በሚገኙ የአስመራ መንገዶች የሚንፈላሰሱ ታክሲዎች የኢትዮጵያ፤ በተለይም የአማርኛ ሙዚቃዎችን እንዲሁም መንፈሳዊ መዝሙሮችን ያጫውታሉ። የከተማዋ የመዝናኛ ማዕከላት ታዳሚዎቻቸውን በአማርኛ ሙዚቃዎች ያስቦርቃሉ።በአማርኛ ቋንቋ የሚሰራጩ ሥነ-ጥበባዊ የቴሌቭዥን መርሃ-ግብሮች በዛ ያሉ ታዳሚዎች አሏቸው። ለአማራኛ የቴሌቭዥን ድራማዎች ልዩ ፍቅር እንዳላቸው ያጫወቱን ወጣቶች ድራማዎቹ የአማርኛ ቋንቋን ለመልመድ እንዳገዟቸውም ጨምረው ነግረውናል።

ከአሥመራ የመጀመሪያ ተጓዦች መካከል የነበሩ ዝነኛ ተዋንያን በኤርትራዊያን አድናቂዎቻቸው ደመቅ ያለ አቀባበልም ተደርጎላቸዋል።

ምንጭ: ቢቢሲ

 

Advertisement

1 Comment

  1. Blood is a lucid transpacific born from the most hospitalized through obtaining (or РІscoringРІ) the common network symposium of malnutrition sedatives (Papaver somniferum). sildenafil pill Smslcq ofdrkc

Comments are closed.