የፊኛ ኢንፌክሽን ምንድን ነው?

የሴት ልጅ ፊኛና የሰገራ መውጫ ቅርብ በመሆኑ በሽታው በአብዛኛው ሴቶችን ሲያጠቃ ምልክቶቹም በድንገት በመከሰት ከኩላሊት ኢንፌክሽን መለየት ይቻላል:: ምልክቶቹም :-
1. በተደጋጋሚ ማሸናት ( ሲከፋ : ሲሸኑ ማቃጠል)
2. ሽንት ለመሽናት ማስቸኮል
3. የፊንኛ ቦታ የመቁረጥና መወጠር ስሜት መሰማት
4. የመድከም ስሜት መሰማት
5. ሲከፋ : በሽንት ውስጥ ደም ማየት
ይህ በሽታ በቀላሉ ማከም ሲቻል በጊዜው በትክክል ካልታከሙ ግን ባክቴሪያው በሽንት አስተላላፊ ቱቦ አማካኝነት ኢንፌክሽኑ ወደላይ በመውጣት ወደ ከፋው የኩላሊት ኢንፌክሽን ይለወጣል:: ምልክቶቹም :- የወገብ ህመም : ትኩሳትና ብርድብርድ ማለት ሲሆን ህክምናውም ጠንካራ መድሃኒት ወይም ባክቴሪያውን ብቻ የሚገድል አንታ- ባዮቲክስ መድሃኒት በአስቸኳይ መውሰድ አስፈላጊ ነው::
የፊኛ ኢንፌክሽን በመከላከል የኩላሊት ኢንፌክሽንና ተደጋጋሚ የፊንኛ ኢንፌክሽን መከላከል ይቻላል::
የበሽታው መነሻ መንስሄዎችና ማባባሻ ምክንያቶች :-
ይህ ኢንፌክሽን በአብዛኛው የሚከሰተው በፊንኛ ውስጥ በሚገኘው ኢኮላይ / E.Coli) በሚባል ባክቴሪያ ሲሆን ይህ ባክቴሪያ ፊኛ ውስጥ ሊጠራቀም የሚችለው:-
1.አብዝቶ ጣፋጭ ምግቦች በመመገብ / ስኳር የበዛባቸው መጠጦች በመጠጣት
1.1 ለአነዚህ ባክቴሪያዎች ጥሩ የምግብ ምንጭ ና መራባት ምክንያት መሆንና
1.2 የተፈጥሮ የበሽታ የመከላከያ አቅም በማሳነስ ለተደጋጋሚ ኢንፌክሽኖች መጋለጥ
2. ያለመጠን ውጥረት / stress / ውስጥ መሆን
3. ትክክለኛ የመፀዳጃ ዘዴ አለመጠቀምና አጠቃላይ ንፅህና ማነስ
4. መጠኑ የበዛ የግብረ ስጋ ግንኙነት ማድረግ
5. ለተለያዩ የባክቴሪያ ኢንፌክሽኖች የሚወሰዱ ፀረ ባክቴሪያ ( አንታይ- ባዩቲክስ/anti-biotics) መዳኒቶች መውሰድ:- በተደጋጋሚ ( ጠቃሚውንም □ጂውንም ባክቴሪያ የሚገሉ -wide spectrum antibiotics :- Bactrim: Amoxcillin: Ampicillin and Cipro ) እነዚህ መዳኒቶች መውሰድ ጠቃሚ ባክቴሪያዎች በማዳከም; □ጂ ባክቴሪያዎች በብዛት እንዲራftና ለተደጋጋሚ ኢንፌክሽኖች መጋለጥ ናቸው::

ምንጭ: ዶክተር አለ

Advertisement

2 Comments

Comments are closed.