ከሁለት አስርት ኣመታት በኋላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአዲስ አበባ ወደ አስመራ የሚያደርገውን በረራ ዛሬ ጀመረ።
በዛሬው ዕለት 465 ተጓዦችን የያዘ ቦይንግ 787 ድሪም ላይነር አውሮፕላን ከአዲስ አበባ ወደ አስመራ በረራውን ያደርጋል።
ከ20 ዓመታት የባላንጣነት ቆይታ በኋላ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ የዛሬ ሁለት ሳምንት የሰላም እና የወዳጅነት የጋራ መግለጫ “የአስመራ ዲክላሬሽን” የተሰኘ ሰነድ ፈርመዋል።
ከአዲስ አበባ ወደ አስመራ የሚወስዱ አውራ ጎዳናዎች
በሰነዱ ላይ ከሰፈሩ ጉዳዮች አንዱ በአንቀፅ 3 ላይ የሰፈረውና በሁለቱ ሀገራት መካከል ተቋርጠው የነበሩት የትራንስፖርት፣ የንግድ እና የኮሚኒኬሽን አገልግሎቶች እንዲቀጥሉ የሚጠይቀው ክፍል ይገኝበታል።
በሁለት አስርት ዓመታት ውስጥ መደበኛ ተጓዦችን ይዞ ወደ ኤርትራ የአየር ክልል ሲሻገር የመጀመሪያው መሆኑ የተነገረለት አውሮፕላን በውስጡ ከፍተኛ የመንግስት ተወካዮች፣ ባለሀብቶች እና ለዓመታት ከቤተሰቦቻቸው ተለያይተው የነበሩ ኤርትራዊያን እንደሚይዝ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዋዜማው አስታውቋል።
በኢኮኖሚ ፣በቢዝነስ እና ቢዝነስ ዴሉክስ በተከፋፋሉት የበረራው አገልግሎቶች ለመጠቀም ተጓዦች ከ11ሺ እስከ 30ሺ ብር መክፈል እንደሚጠበቅባቸው ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ድረ-ገፅ ለመረዳት ችለናል።
በረራው ከመደረጉ ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ወደ ኤርትራ ከሚያደርሱ አምስት የአየር መስመሮች መካከል አንዱን በጊዜያዊነት መክፈቱን ለሀገር ውስጥ የመገናኛ ብዙሃን አስታውቋል።
የዛሬው በረራ የሚደረገው UM308 ተብሎ በሚጠራው ከኬንያ -አዲስ -አበባ- መቀሌ አድርጎ አስመራ በሚያደርሰው የአየር መስመር በኩል መሆኑ ታውቋል።
እንዲህ ያለው እርምጃ በሁለቱ ሀገራት መካከል የነበረው ጦርነት ነጣጥሏቸው የነበሩ ቤተሰቦችን፣ የትዳር ተጣማሪዎች እና ህዝቦችን ለማገናኘት «በጣም ጠንካራ ድልድይ » መሆኑን የጠቀሱት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገ/ማሪያም ፤ አየር መንገዱ የሁለቱን ሀገራት ህዝቦች ከማገናኘት አልፎ ከኤርትራ አየር መንገድ ጋር አብሮ ለመስራት ፍላጎት እንዳለውም ለቢቢሲ ተናግረዋል።
የመንግሥት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሃላፊ ሚንስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ ትናንት ረፋድ በትዊተር ገጻቸው ላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኤርትራውን አየር መንገድ 20 በመቶ ድርሻ ሊገዛ እንደሆነ ገልጸዋል።
በፈረንጆቹ 1991 ዓ.ም ተቋቁሞ በ2003 ዓም የንግድ በረራ የጀመረው የኤርትራ አየር መንገድ ያን ያህል የስኬት ታሪክ የለውም።
አየር መንገዱ በአሁኑ ሰዓት ወደ ካርቱም፣ ካይሮ፣ ጂዳ፣ ዱባይ እና ሚላን በሳምንት ከ3-5 ጊዜ በረራ ያደርጋል።
ከ2012 ጀምሮ ወደ አውሮፓ ህብረት ሀገራት በረራ እንዳያደርጉ እግድ ከተጣለባቸው አየር መንገዶች መካከል አንዱ ነው።
ምንጭ: ቢቢሲ
History on it’s Best up-close!!
God is Love♥️
Love is God ♥️
Geta mesgana Ygbahe
Thank you PE
God bless you
Like!! I blog quite often and I genuinely thank you for your information. The article has truly peaked my interest.
I like the valuable information you provide in your articles.
These are actually great ideas in concerning blogging.
I like this website very much, Its a very nice office to read and incur information.
I used to be able to find good info from your blog posts.
fake rolex for sale at low prices.
It remains calm cialis online system. sildenafil without a doctor prescription Uopnkv fbfmlp