NEWS: የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በጎ አንደበትና የኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳር

ኢትዮጵያ የተለየ የፖለቲካ ማዕበል ውስጥ ናት። አበይት ፖለቲካዊ እርምጃ በተወሰደባቸው ሦስት ወራት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለማመስገን በተዘጋጀው የድጋፍ ሰልፍ ያጋጠመው የቦንብ ፍንዳታ፣ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሚታዩ ግጭቶች፣ ያልተረጋጉ የፖለቲካ ጥያቄና እስከ አሁን አገራዊ መግባባት ሊደረስበት ያልቻለው የሰንደቅ አላማ ጥያቄ በተለያየ አጋጣሚ እየተንጸባረቁ ናቸው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ሥልጣን ከመጡ ወዲህ በአገር ውስጥም ሆነ ከአገር ውጪ በእስር የነበሩ ሰዎች ማስፈታት፣ የተዘጉ የህትመትና ኤሌክትሮኒክስ መገናኛ ብዙኃንን መክፈት፣ የአገሪቷን ወሳኝ ቦታዎች ተቆጣጥረዋል የተባሉትን የደህንነትና የመከላከያ አመራሮች በሌሎች መተካት፣ ለ20 ዓመታት የተቋረጠውን የኢትዮ- ኤርትራ ግንኙነት ለውይይት ክፍት ማድረግ የመሳሰሉትን አበይት ፖለቲካዊ እርምጃዎች በመውሰድ አገር የማረጋጋት ስራውን የጀመሩባቸው 100 ቀናት ተቆጠሩ።

ታዲያ እነዚህ እርምጃዎች ፖለቲካዊ ምህዳሩ አሰፉ ወይስ እጅግ ፈጠኑ? ያኮረፉትን አባብለዉ አዲስ አኩራፊ ሃይል ፈጠሩ ወይስ የተጣመመውን ማቅናት ቻሉ?

“መንግሥት የሚደግፈው የሙስሊሙን ሕብረተሠብ ነው” ጠ/ሚኒስትር ዐብይ አህመድ

ጠ/ሚ ዐብይ አልበሽርን የድንበር ግጭቱን አብረን እንፍታ አሉ

በግብጽ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ

“በትግራይ ስም እንደራጅ እንጂ የኛ አመለካከት ቀድሞውንም ኢትዮጵያዊ ነው” ዶክተር አረጋዊ በርሔ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ለአፋር የሀገር ሽማግሌዎች ሰላምታ ሲሰጡImage copyrightFITSUM AREGA TWITTER PAGE

“እየነጋ ያለ ይመስለኛል”

በሽብርተኝነት ተከሶ 2011 ላይ የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶበት በእስር የቆየዉ አንዱዓለም አራጌ በይቅርታ ከተፈቱ እስረኞች መካከል አንዱ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እያደረጓቸው ያሉት በጎ ንግግሮች የሚመሰገኑ ናቸዉ የሚለው አንዱዓለም አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ እየታየ ያለውን ፖለቲካዊ ለውጥ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት ደረጃ በደረጃ እየተፈጸሙ እንዳሉ የሚያሳዩ ለውጦች ናቸዉ ሲል ይገልፀዋል።

“አሁን ላይ ንጋት ነው የማየዉ” የሚለው አንዱዓለም በጠቅላይ ሚኒስትሩ እየተወሰዱ ያሉትን እርምጃዎችና የገቡትን ቃል የሚመሰገን ነው ይላል።

“ምናልባት እየነጋ ይመስለኛል። የኢትዮጵያ ህዝብ መቃወም ብቻ ሳይሆን የሚደገፍ ሃሳብና ሰው ሲገኝ መደገፍ እንደሚችል ደግሞ እያሳየ ነዉ። ተቃዋሚው ሁሉ ሲቃወም፣ ሲታሰር ሲፈታ የነበረው የሚደገፍ ሃሳብ በማጣቱ እንደሆነና ኢትዮጵያውያን ምክንያታዊ እንደሆንን የሚያሳይ ነው” ሲል ይገልጸዋል።

እየተካሄደ ያለው ለውጥ መጀመሪያም ህገ መንግሥቱ ላይ የነበሩና በረጅም ሂደት በመመሪያ፣ በደንብ፣ በፖሊሲ አንዳንዴም በጉልበትና በውሳኔ እየተጨፈለቁና እየተደመሰሱ የመጡ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀ መንበር የነበረው አቶ ሙሼ ሰሙ ይናገራል።

“ጠቅላይ ሚኒስትሩ ህገ መንግስቱ ላይ የሰፈሩ ሰብዓዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች እንዲከበሩ፣ ያለ ፍርድ ቤት መታሰርና ያለ ጠያቂ መቅረት፣ መገረፍና አካል መጉደል የመሳሰሉት ህገ መንግስቱ የማይደግፋቸው ድርጊቶችና ሃሳቦች እንዲቀለበሱ ነው ያደረገው” ይላል።

በኢትዮጵያ በስርዓት ውስጥ ለውጥ መምጣቱን የሚናገረዉ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ ስራ አስኪያጅ ጃዋር መሀመድ በበኩሉ የፖለቲካ ምህዳሩ እየሰፋ እንዳለ ለቢቢሲ ተናግሯል።

“ወደ ዲሞክራሲ የምናደርገው ሽግግር በፍጥነት እየተካሄደ ነው። በተለይ ደግሞ እየተደረገ ላለው ሽግግር ምሁራዊ እርዳታ ማድረግ ያስፈልጋል። ገዢው ፓርቲ ላይም ጫና በመፍጠር ሽግግሩ በፍጥነት እንዲሄድና የተቃውሞ ኃይሉም በፍጥነት እየተዘጋጀ ለሽግግሩ አቅሙ እየጎለበተ እንዲሄድ ማድረግ አስፈላጊ ነው” ሲል የአገሪቷን የፖለቲካ ምህዳር የሚሰፋበት መንገድ አመላክቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ከኤርትራ ልዑካን ቡድን አባል ጋር በቦሌ አየር ማረፊያImage copyrightFITSUM AREGA TWIITER PAGE

ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጣፋጭ አንደበት ባሻገር

በሃሳብም ነፍጥ በማንሳትም ለመታገል ከአገር ተሰደው በጎረቤት አገሮች፣ በአውሮፓ እና በአሜሪካ ከትመው የነበሩ ኃይሎች ወደ አገር ቤት ገቡ። በርካቶችም ከእስር ተፈቱ።

“ሽብርተኛ” የተባሉትም ጥላሸት የተቀባው ስማቸዉ ተገፎ በነጻነት መታገል እንደሚችሉ ጥሪ ቀረበላቸው። ሆኖም ግን አሁን ያለው የፖለቲካ ምህዳር ዝብርቅርቅ ያለ ነው የሚለው አቶ አንዱዓለም ነገሮች መልክ ይዘው እየሄዱ አይደለም ሲል ይናገራል።

“በአንድ በኩል ሀሳቦች እንዲንሸራሸሩ ሰው ነጻ ሆኖ እንዲናገር የሚል ይፋዊ የሆኑ መግለጫዎች አሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ ብዙ ጊዜ ሲታገል የነበረው የኢትዮጵያ ህዝብ መብቱ እንዲከበር ከፍተኛ ፍላጎት አለ። እነዚህ ነገሮች ግን መልክ በያዘ መንገድ ሳይሆን አየር ላይ ሲንሳፈፉ ነው የሚታየኝ” ይላል።

“መንግሥት በዚህ ጉዳይ ያለው ቁርጠኝነት በጽሁፍ፣ በአዋጅ ተደግፎ የጸደቀ አይደለም። ከጠቅላይ ሚኒስትሩ በጎ አንደበት ውጪ መልክና ቅርጽ የያዘ ነገር የለም። በሁለቱም አቅጣጫ አየሩ ገና የነጻነት አየር እየሞቀ ያለ ነው። ያ ግን ምን ድረስ ይሄዳል፣ የሚገድቡ ነገሮችስ ይኖሩ ይሆን የሚለው ግልጽ አይደለም፤ ውዥንብር አለው” ሲል ይገልጸዋል።

የክርስቲያን የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራትና ህብረት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሸሻ ሸዋረጋ ደግሞ “በዚህ የፖለቲካ ምህዳር የማስፋት ጉዞ የወጣቶች፣ ሴቶች፣ ህጻናትና አካል ጉዳተኞች መብት ማስከበር፣ ግጭቶች መፍታት፣ከበጎ አድራጎት ድርጅቶች ጋር በተያያዘ የተቀመጡ ድንጋጌዎች ይሻሻላሉ ብለን እናስባለን” ይላሉ።

“በሰብዓዊ መብት ጥበቃ ዙርያ፣ ዜጎች እንዲጠይቁ ስለሚያስችሉ የዲሞክራሲ ግንባታን የሚያፋጥኑ ብቻ ሳይሆን ዜጎች መንግሥትን እንዲጠይቁ ስለሚሰሩ የዲሞክራሲ ምህዳሩን ያሰፋዋል ብለን ተስፋ እናደርጋለን” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ከዚህ ባለፈ ይላሉ ዶክተር መሸሻ “የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ዜጎች ህገ መንግስቱ የሰጣቸውን መብት እንዲጠቀሙ የተለያዩ ስልጠናዎች ሲሰጡ፣ ምርጫ ላይም ሲሳተፉ ነበር። አዋጁ ከወጣ በኋላ ከተከለከሉ ነገሮች አንዱ ግን ይህ ነው፤ ይህ ከተሻሻለ ያለመሸማቀቅ መብታቸው ስለሚያረጋግጥላቸው ወደ ፊት በዲሞክራሲያዊ ምህዳር ማስፋት ትልቅ ስራ እንዲሰሩ ያስችላቸዋል” ሲሉ ያክላሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ገለፃ ሲሰጡImage copyrightANADOLU AGENCY

ያዋከቡት ነገር ምዕራፍ አያገኝም…

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ውሳኔዎች ፈጠኑ የሚሉ ሰዎች ድምፅ ይሰማል። ከውሳኔያቸው መፍጠን የተነሳ የራሳቸው እርምጃ እንቅፋት እንዳይሆኑባቸው ስጋታቸውን የሚያስቀምጡም አሉ።

“ለረዝም ጊዜ ሲወድቁ ሲነሱ የነበሩ አጀንዳዎች ስለሆኑ ፈጠኑ የሚባሉ አይመስለኝም” የሚሉት ዶክተር መሸሻ ከፍተኛ ጥያቄ ሲነሳባቸው የነበሩ አዋጆችና ሲገፉ የነበሩ ጉዳዮች ስለሆኑ የተወሰደው እርምጃ የሚደነቅ ነው ይላሉ።

“ሆኖም ግን ተጀመረ እንጂ አልተጠናቀቀም። የእነዚህ አዋጆች ለውጥ እስከ ምን ድረስ ነው? የሚለው ገና ነው። አካራካሪና ሲያነታርኩ የነበሩ ነገሮች በምን ያክል አድማስ ይለወጣሉ? የሚል በተስፋ ከመጠበቅ ይልቅ ጮቤ የሚያስረግጥ አይደለም” ሲሉ ይናገራሉ።

“የተቻኮለ ነገር የለም” የሚለው አቶ ሙሼ በበኩሉ የነበረዉ ስርአት ኣልበኝነት ወደ ስርአት እንዲመጣ አስደናቂ ሥራዎች መሥራት ግድ ይል ስለነበር የተሰራዉ ስራ ትክክል ነው ይላል።

እዚህ ሂደት ላይ ያለው ፍጥነት ያሰጋኛል የሚለው የኦሮሚያ ብሮድካስት ኔትዎርክ ስራ አስኪያጅ ጃዋር መሀምድ መሰረት መያዝ እንዳለበት ይመክራል።

“ከስር ከስር መሰረት እየያዘ፣ እየተጠናከረ ስላልሄደ ለውጡ እየሄደበት ያለው ፍጥነት ያሳስበኛል። ፍጥነት ጥቅም እንዳለው ሁሉ ስጋትም አለው። በቀጣይነት የምሁራንና የተለያዩ ሰዎች ተሳትፎ ያስፈልጋል።”

“እየሄድንበት ያለዉ መንገድ ለመለወጥ ጥረት እያደረግንበት ስለሆነ ከዚህ ሃሳብ ተቃራኒ ቆመናል የሚሉ ሃይሎች መድረክ ላይ በመቅረብ የማሸነፍና የመሸነፍ ልምድ መዳበር አለበት፤ መድረክ አለ ማለት ብቻ ግን በቂ አይደለም” ይላል አቶ ሙሼ ሰሙ።

ጃዋር መሀመድም አሁን አገሪቷ ውስጥ እዚህም እዛም የሚታዩ አለመረጋጋቶችና ግጭቶች ቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች መሆናቸውን ያሰምርበታል።

ምንጭ: ቢቢሲ

Advertisement

1 Comment

  1. To stalk and we all other the earlier ventricular that buy corporeal cialis online from muscles still with still essential them and it is more average histology in and a hit and in there acutely useful and they don’t equable termination you are highest trick off on the international. sildenafil 100 Iuzqpr mutpcl

Comments are closed.