NEWS: ከዚምባብዌ ጥቃት በስተጀርባ ግሬስ ሙጋቤ?

የዚምባብዌ ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋጓን በፍንዳታው የሚጠረጠሩት ሰዎች ከቀድሞዋ ቀዳማይ እመቤት ጋር ግንኙነት ያላቸው ቡድኖች ሊሆኑ እንደሚችሉ ጠቁመዋል።

በፍንዳታው ሁለት ሰዎች ሞተው ከ40 በላይ ሰዎች ጉዳት እንደደረሰባቸው ይታወቃል።

ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋጓ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የቀድሞዋን ቀዳማይ እመቤትን ፕሬዝዳንት እንድትሆን የሚደግፈው “ጂ40” የተባለ ቡድን ጥቃቱን ፈጽሟል ብለዋል።

ግሬስ ሙጋቤ ከሥልጣን የወረዱት ባለፈው ዓመት ነበር።

ሙጋቤ ከሥልጣን ከመውረዳቸው አስቀድሞ ባለቤታቸው ግሬስ ይተኳቸዋል የሚለው ወሬ በሰፊው መናፈሱ ወታደሩ ጣልቃ እንዲገባ ምክንያት ከሆኑት ነገሮች መካከል አንዱ ነው።

ፕሬዝዳንት ምናንጋጓ ጥቃቱ ከተፈፀመ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰጡት ቃለምልልስ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር የማዋል እርምጃው በቅርቡ እንደሚጀመር ገልፀዋል።

“አንድ ሰው መሆኑን አላውቅም፣ ከአንድ ሰው በላይ ተሳትፎበታል ብዬ አስባለሁ፥ ይህ በከሰሩ ፖለቲከኞች የተወሰደ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ እንደሆነ አስባለሁ” ብለዋል።

በወቅቱ ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩት ምናንጓጋዋ እና ግሬስ ሙጋቤ፣ ሮበርት ሙጋቤን ይተኳቸዋል ተብለው ከሚጠበቁት መካከል ነበሩ።

ግሬስ ሙጋቤን የሚደግፈው አንጃ ጂ 40 ይሰኛል። ሆኖም ፕሬዚዳንቱ ግሬስ ሙጋቤ ከጥቃቱ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አላቸው የሚል ክስ አላቀረቡም።

ምንጭ: ቢቢሲ

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.