NEWS: Australian court fines Apple $6.7 million over iPhone ‘bricking’ case | የአውስትራሊያ ፍርድ ቤት በአፕል ኩባንያ ላይ የ6 ነጥብ 7 ሚሊየን ዶላር ቅጣት ወሰነ

ግዙፉ የቴክኖሎጅ ኩባንያ አፕል በአውስትራሊያ ፍርድ ቤት የገንዘብ ቅጣት ተጥሎበታል።

ኩባንያው 6 ነጥብ 7 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገንዘብ ቅጣት ነው የተላለፈበት።

የኩባንያው ደንበኞች በገዙት አይ ፎን ስልክና አይ ፓድ ላይ ለደረሰው ጉዳት የዋስትና ጥገና አልሰጥም ማለቱን ተከትሎ ቅጣቱ ተጥሎበታል ነው የተባለው።

የተባለው ችግር የተፈጠረው የኩባንያው ደንበኞች በገዟቸው የኤሌክትሮኒክስ ምርቶች ላይ ሶፍትዌር ላይ ከጫኑ በኋላ ስልኩ መስራት ያቆማል።

በዚህ ጊዜም ኩባንያው ለተፈጠረው ችግር አፋጣኝ መፍትሄ ይሰጣቸው ዘንድ ጥገና እንዲፈቀድላቸው ይጠይቃሉ።

ኩባንያው ግን የተባለው የኤሌክትሮኒክስ እቃ ከአፕል ውጭ ባሉ ተቋማት አማካኝነት ጥገና የተደረገለት በመሆኑ ለተፈጠረው ችግር ሃላፊነት አልወስድም ብሏል።

ይህን ተከትሎም ደንበኞች ጉዳያቸውን ለአውስትራሊያ የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ኮሚሽን አሳውቀው ኩባንያው ክስ ይመሰረትበታል።

የሃገሪቱ የንግድ ውድድርና ሸማች ኮሚሽንም ኩባንያው የንግድ ውድድርና ሸማች ህጉን ጥሷል በሚል ኩባንያውን ከሷል።

ኩባንያውም ቢሆን 275 ደንበኞቹን በገዙት እቃ ላይ ስላላቸው መብት ከህጉ ጋር በሚጣረስ መልኩ ምላሽ መስጠቱን አምኗል።

ጉዳዩም በሃገሪቱ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሲታይ ቆይቶ ኩባንያው ጥፋተኛ በመሆኑ የገንዘብ ቅጣቱ ተወስኖበታል።

የዚህ ሰለባ የሆኑ 275 ደንበኞቹም በውሳኔው ተጠቃሚ ይሆናሉ።

አፕል ከዚህ ቀደምም በደንበኞቹ ላይ ለተፈጠረ ችግር እቃዎቹን ለሶስተኛ ወገን አሳይቷችኋል በሚል ለተጠቃሚዎች መስጠት የሚገባውን ዋስትና መከልከሉ ይነገራል።

ምንጭ: ኤፍ ቢ ሲ(FBC)

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.