NEWS: Boat Carrying Eritrean Refugees Reaches Spain | ኤርትራዊያን ስደተኞችን ያቀፈቸው መርከብ ስፔን ደርሳለች

 

 

 

በርካታ ስደተኞችን አቅፋ ሜድራንያን ባህር ላይ ስትኳትን የነበረችው አኳርዬስ የተሰኘች መርከብ በስተመጨረሻም በስፔን በጎ ፈቃድ ቫለንሲያ ከተማ ደርሳለች።

ባለፈው ሳምንት ነበር በርካታ ስደተኞችን አቅፋ ሜዲትራንያን ባህር ላይ ስትዳክር የነበረችው መርከብ ወደ ጣልያን ወደብ ያመራቸው፤ ምንም እንኳ የጣልያን ባልሥልጣናት ፊት ቢነሷትም።

630 ስደተኞችን አሳፍራ ስትጓዝ የነበረችው ይህች መርከብ ቀጣይ ጉዞዋን ወደ ማልታ ብታደርግም ተመሳሳይ ዕጣ ፈንታ ነው የገጠማት።

የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ማሕበር እንዲሁም መሰል ጉዳዩ ይመለከተናል ያሉ ተቋማት መርከቧ ማረፊያ ታገኝ ዘንድ ሲሟገቱ ነበር።

በስተመጨረሻም አዲሱ ሶሻሊስት መንግሥት ስደተኞቹን ተቀብሎ ተገቢውን እንክብካቤ ለማድረግ ቃል ገብቷል።

“የሰው ልጅ ላይ የሚደርስ ጉዳትን ለማስወገድ የበኩላችንን አስተዋፅኦ ማድረግ ግዴታችን ነው፤ ከሰብዓዊ መብት ህግጋታችንም ጋር አብሮ የሚሄድ ድርጊት ነው” ሲሉ ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ ተናግረዋል።

ስደተኞቹ ከ26 ሃገራት እንደመጡ ሲታወቅ ከሱዳን እና ናይጄሪያ 300 ያህል ሰዎች እንዲሁም ቁጥራቸው ላቅ ያለ ኤርትራዊያን መርከቧ ላይ እንደነበሩ ሊታወቅ ችሏል።

ከአፍጋኒስታን፣ ፓኪስታንና ባንግላዴሽ የመጡ ስደተኞችም መርከቧን አጨናነቀዋት እንደነበር ተዘግቧል።

ከሳምንታት እንግልት በኋላ መሬት የረገጡት ስደተኞቹ አስፈላጊው እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሆነም ቢቢሲ ተገንዝቧል።

ምግብ፣ አልባሳትና እና ማረፊያ ቦታ የተመቻቸላቸው ሲሆን ነብሰ-ጡር ሴቶች ደግሞ ወደ ጤና ማዕከል ተወስደዋል።

ለጥቆማ አስፈላጊው ምርመራ ተካሂዶላቸው ወደመረጡት እንዲሁም ፈቃደኛ ወደሆኑ ሃገራት የሚሄዱበት ሁኔታ እንደሚመቻችላቸው ታውቋል።

የጣልያን ድርጊት “ኃላፊነት የጎደለው” ነው ሲሉ የወቀሱት “የፈረንሳዩ ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን ስደተኞቹን ተቀብሎ በማስተናገድ ዙሪያ ከስፔን ባልሥልጣናት ጋር እንደመከሩ አሳውቀዋል።

ምንጭ: ቢቢሲ

Advertisement

1 Comment

Comments are closed.